የከተማ ቦታ ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
42

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለ1ኛ (አንደኛ) ዙር የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 መሰረት ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ 20 ቦታዎችን በመደበኛ የከተማ ቦታ ሊዝ ጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የከተማ ቦታ በሊዝ መጫረት የምትፈልጉ ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል አማኑኤል ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት አገልግሎት አሰጣጥ ቡድን ቢሮ  በመቅረብ  ሰነድ መግዛት እና መጫረት ይችላሉ፡፡

  1. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት መጀመሪጠያው የሥራ ቀን ጀምሮ ጨረታው በጋዜጣ ከቆየበት እስከ 10 (አስረኛው) የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ድረስ ይሆናል፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃው ጨረታው በጋዜጣ ከቆየበት በ10 (አስረኛው) የስራ ቀን ከቀኑ 10፡00 ላይ ይሆናል፡፡
  3. የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው (የሚታሸገው) ጨረታው  በጋዜጣ ከቆየበት በ10 (አስረኛው) የሥራ ቀን  ከቀኑ 11፡00 ላይ ይሆናል፡፡
  4. ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎች የጉብኝት ፕሮግራም በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ይሆናል፡፡
  5. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11 (አስራ አንደኛው) የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ላይ በአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጨረታው በጋዜጣ ከቆየበት 11 (አስራ አንደኛው) ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ግን ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን  የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here