የከተማ ቦታ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
83
  1. የጨረታ ዙር፡ የ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ጨረታ
  2. የጨረታዉ ዓይነት፡ መደበኛ ጨረታ
  3. የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረዉ መሰረት ለመኖሪያ 20 (ሃያ) ቦታዎች ለድርጅት (የሆቴል) 7(ሰባት) የተዘጋጁ ቦታዎችን በመደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛዉም 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው ኢትዮጵያዊ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ22/07/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለመኖሪያ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/  ለድርጅት ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ከ/መ/ል/ባ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 004 ዘወትር በሥራ ቀን እስከ 11፡00 መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታወቃለን፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቀኑ እስከ 11፡00 ብቻ ይሆናል፡፡
  5. ጨረታዉ የሚዘጋዉ ሰነድ ሽያጭ ባለቀበት ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
  6. ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎችን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ በኋላ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ከባለሙያ ጋር መጐብኘት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከታሸገበት በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የመኖሪያ በቀጠዩ ቀን የድርጅት በእን/ከ/አስተዳደር አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  8. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 251 058 227 00 05 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ ከተማ አስተዳድር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here