የሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በ2017 በጀት አመት 1ኛ ዙር ጨረታ የድርጅት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለአሸናፊዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ከ04/09/2017 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 /አስር/ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዘር መረጃና የጨረታ ሰነድ ሀሙሲት ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት የማይመለስ ብር ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ብቻ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን በ11፡00 የሚዘጋ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ቦታው በሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ግቢ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ መመልከትና በስልክ ቁጥር 058 443 00 62 ወይም 058 443 04 94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሀሙሲት ከተማ አስ/ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት