የከተማ ቦታ የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

0
62

የሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለማስያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በ2018 በጀት አመት 1ኛ ዙር ጨረታ የድርጅት ቦታዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለአሸናፊዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፦

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ታህሳስ 06/2018 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ ሀሙሲት ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ብቻ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን በ11፡00 የሚዘጋ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ሳጥኑ ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ቦታው በሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ግቢ ይሆናል፡፡
  5. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  6. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ በሰሌዳ ላይ መመልከትና በስልክ ቁጥር 058 443 00 62 /04 94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሀሙሲት ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here