የባሕር ዳር ዓባይ ወንዝ ሚሊኒዬም ፓርክ ከጣና ኃይቅ ደቡባዊ ጫፍ የዓባይ ወንዝ መውጫ እስከ ጢስ ዓባይ ፏፏቴ ድረስ በወንዙ መውረጃ ግራ እና ቀኝ የሚገኘውን ቀጣና የሚሸፍን ነው፡፡ የፓርኩ አጠቃላይ ስፋትም 4680 ሄክታር ተለክቷል፡፡
ከጣና ኃይቅ 25 ወይም (28) ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የዓባይ ወንዝ ከሚደርስበት ከ400 ሜትር ስፋት ከገደሉ ቁልቁል 50 ሜትር ይወረወራል፡፡ በማረፊያው ወለል የሚፈጥረው ህብረ ቀለምም ቀልብ የሚገዛ መስህብ ነው የጢስ ዓባይ ፏፏቴ፡፡
የቀጣናው የዓየር ንብረት ከ2009 እስከ 2019 እ.አ.አ ባሉት 10 ዓመታት ከተሰበሰበው መረጃ ከየወሩ አማካይ ዝቅተኛው ሰባት ነጥብ ዘጠኝ ከፍተኛው በአማካይ 30 ነጥብ ሁለት ሴልሺዬስ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
በዝናብ መጠን አማካዩ 1461 ነጥብ ሁለት ሚሊ ሜትር ሲሆን ከፍተኛ የዝናብ መጠን የተመዘገበባቸው ወራት ደግሞ ከሰኔ እስከ መስከረም ያሉት ወራት ናቸው፡፡ መጋቢት እና ሚያዚያ ደግሞ ዝናብ የሌላቸው ወራት ሲሆኑ የዓባይ የወንዙ የውኃ መጠንም አነስ ያለ ነው፡፡
ከፓርኩ ክልል 1352 ሄክታር ወይም 28 ነጥብ 58 በመቶ በባህር ዛፍ ደን፣ የግጦሽ መሬት ወይም በሳር የተሸፈነው ደግሞ 1235 ሄክታር ወይም 26 በመቶ ያህሉ ነው፡፡
ከዓባይ ወንዝ ደርቻ በቤዛይት ደን 48 የእፅዋት ዝርያዎች በፓርኩ ውስጥ እንደሚገኙ ተመዝግቧል በቀጣናው ለሚገኙ ኗሪዎች በገቢ ምንጭነት የባህር ዛፍ ደን በስፋት ለመቶ ይታያል፡፡
የፓርኩ ከፊል ቀጣና በረግረግ ዳርቻዎች በመስኖ ልማት አትክልት እና አዝርእት ይለማባቸዋል፡፡
ለፓርኩ ዘላቂነት በስጋትነት ከተጠቆሙት ከከተማ እንዲሁም ከፋብሪካዎች የሚለቀቅ በካይ ፍሳሽ ተጠቅሷል፡፡
በአጠቃላይ በባሕር ዳር የዓባይ ወንዝ ሚሊኒዬም ፓርክን ተፈጥሯዊ ስነምህዳሩን ለእርሻ መሬት ለማስፋፋት እና ለማገዶ የደን መመንጠር በእጅጉ የቀየረው መሆኑ በማደማደሚያነት ለንባብ በቅቷል፡፡
ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት አፍሪካን ሳፊሪ ኦኘሬተርስ፣ ባዮ ሜዲሴንትራል፣ ፊልም ፊክሰር ድረ ገፆችን ተጠቅመናል፡፡
(ታምራት ሲሳይ)
በኲር የመጋቢት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም