የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ከሎት 1 እስከ ሎት 4 የእቃ አቅርቦቶችን ማለትም፡- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ሎት 2 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 3 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ሎት 4 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸዉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የሚገዙ የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ00 /አምሳ ብር/ ብቻ መግዛት የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት አቅርቦት ጠቅላላ ድምር ውጤት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ አንድ በመቶ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅ ፖስታዎች ማለትም ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማዕ/ጎን/ዞን/ማረ/ቤቶች መምሪያ ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ከጥር 05/2017 እስከ ጥር 19/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ሰነድ መግዛት ይኖርባችኃል፡፡
- ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ሆነ ባይገኙም ጨረታዉ በሰዓቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ጥር 20/2017 ዓ.ም በ4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ስለ ጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 211 98 76 ወይም በሞባይል ቁጥር 09 64 79 28 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማዕከላዊ ጎንደር ማረሚያ ቤቶች መምሪያ