የዜሮ መቻቻል ቀን

0
90

የሴት ልጅ ግርዛት የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ለማስቀረት እ.አ.አ የካቲት 06 ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል። የዘንድሮውም የዜሮ መቻቻል ቀን (FGM) በሚል በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል። እስከ 2030 ድረስ የሴት ልጅ ግርዛትን የማስቆም ዕቅድም ተይዛል። በሴት ልጅ ግርዛት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የመብትና አዕምሯዊ ጉዳት ማስቀረት ደግሞ ግቡ ነው።

የሴት ልጅ ግርዛት በበርካታ የዓለማችን ሃገራት የተከለከለ ተግባር ቢሆንም አሁንም በየቀኑ በበርካታ ሃገራት ይፈጸማል። በየዓመቱ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴት ልጅ ግርዛት የዜሮ መቻቻል ቀንም ታዲያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች እና ልጃገረዶች ሕይወት ላይ ተዕጽኖ እያሳደረ ያለውን  ጎጂ ተግባር ለማስወገድ እና የተቀናጀ እርምጃ ለመውሰድ ዕድል ይሰጣል።

የሴት ልጅ ግርዛት እንዲፈጸም  ከሚዳርጉ ምክንያቶች መካከል የማሕብረሰብ ባሕል፣ ከንጽህና ጋር የተያያዘ የተሳሳተ እሳቤ፣ ድንግልናን ለማቆየት በማሰብ፣ ሴት ልጅ ትዳር እንድታገኝ በማሰብ እና የወንድ ልጅ የወሲብ እርካታን ለመጨመር የሚሉ ምክንያቶች ይገኙበታል።

የሴት ልጅ ግርዛት  የሴቶችን መሠረታዊ (ሰብዓዊ) መብቶች የሚጥስ ጎጂ ድርጊት ነው። በሴት ብልት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከሕክምና ውጪ በሆኑ ምክንያቶች ከአጭር ጊዜ እስከ የዕድሜ ልክ የጤና እክሎችን ያስከትላል። በአካል እና በአዕምሮ ጤና ላይ፣ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ፣ የመራቢያ ዓመታት እና እስከ እርጅና ድረስ የሚዘልቅ ጉዳትም ሊያስከትል ይችላል።

እስከ ዛሬ ድረስ ከ230 ሚሊዮን በላይ ልጃገረዶች እና ሴቶች በግርዛት ምክንያት መጎዳታቸዉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ያመላክታል። አራት ሚሊዮን የሚጠጉ ሴቶች ደግሞ በድርጊቱ ምክንያት በየዓመቱ ጉዳት እንደሚደርስባቸዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ይጠቁማል።

እ.ኤ.አ የካቲት 6 ቀን 2026 የሴት ልጅ ግርዛትን የዜሮ መቻቻል ቀን (FGM) ተብሎ ይከበራል። በዚሁም እስከ 2030 ድረስ የሴት ልጅ ግርዛትን የማስቆም እቅድ ተይዛል ። ይህም በሴት ልጅ ግርዛት ምክንያት በሴቶች ላይ የሚደርሰውን የመብትና አእምራዊ ጉዳትን ለማስቀረት ያስችላል።

የሴት ልጅ ግርዛት በበርካታ የዓለማችን ሃገራት የተከለከለ ተግባር ቢሆንም አሁንም በየቀኑ በተለያየ ሃገራት ይፈጸማል።

በየዓመቱ የካቲት 6 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የሴት ልጅ ግርዛት የዜሮ መቻቻል ቀን  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሴቶች እና ልጃገረዶች ህይወት ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ያለውን ይህን ጎጂ ተግባር ለማስወገድ እና የተቀናጀ እርምጃ ለመውሰድ እድል ይሰጣል።

የሴት ልጅ ግርዛት ከሚፈፀምባቸው የተሳሳቱ ምክንያቶች መካከል የማህብረሰብ አስተሳሳብ፣ ኃይማኖት፣ ከንጽህና ጋር የተያያዘ የተሳሳተ ዕምነት፣ ድንግልናን ለማቆየት በማሰብ፣ ሴት ልጅ ትዳር እንድታገኝ በማሰብ እና የወንድ ልጅ የወሲብ እርካታን ለመጨመር የሚሉ ምክንያቶች ይገኙበታል።

የሴት ልጅ ግርዛት  የሴቶችን መሰረታዊ መብቶች የሚጥስ የሰብአዊ መብት ጥሰት ነው። በሴት ብልት ላይ የሚደርሰው ጉዳት ከህክምና ውጭ በሆኑ ምክንያቶች ከአጭር ጊዜ እስከ የዕድሜ ልክ የጤና ተጽእኖዎች በአካል፣ በጾታዊ እና በአዕምሮ ጤና ላይ፣ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ፣ የመራቢያ ዓመታት እና እስከ እርጅና ድረስ ሊደርስ ይችላል።

የሴት ልጅ ግርዛት በርካታ የጤና፣ የአዕምሮ፣ የአካል እና ስነ ልቦና ጉዳቶችን ያስከትላል። ግርዛቱ በጤና ባለሙያዎች ባለመሆኑና ቅድመም ሆነ ድህረ ጥንቃቄ ስለማይደረግ የሚገረዙ ሴቶች ላይ ከፍተኛ ሕመም እና የደም መፍሰስ፣ ድንጋጤ፣ የሽንት ማለፍ ችግር፣ ኢንፌክሽኖች፣ በብልት ዙሪያ የሚደርስ ጉዳት አለፍ ሲልም ሞት ሊያስከትል ይችላል።

በዚህ ድርጊት እስከ ዛሬ ድረስ ከ230 ሚሊዮን በላይ ልጃገረዶች እና ሴቶች በግርዛት መጎዳታቸዉን እና ጉዳቱም ዘርፈ ብዙ በመሆኑ ድርጊቱን ማስቆም ካልተቻለም  በቀጣይም እስከ እ.አ.አ 2030 ድረስ 22 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ተጨማሪ ልጃገረዶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መረጃ ይጠቁማል።

የሴት ልጅ ግርዛት ባለፉት 30 ዓመታት ወዲህ መጠኑ እየቀነሰ እና መሻሻል ያሳየ ቢሆንም ጨርሶ ማጥፋት ግን አልተቻለም። በመሆኑም በ2030 በዓለም ላይ ድርጊቱን ለማስቆም በተያዘዉ የዘላቂ ልማት ግብ መሰረት የመከላከል ተግባሩን በ27 እጥፍ እና ፈጣን ማድረግ አስፈላጊ  መሆኑን ነዉ ያስቀመጠዉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለው ምንም እንኳ የሴት ልጅ ግርዛት በበርካታ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት ውስጥ በሕግ የተከለከለ ቢሆንም በ24 ሃገራት ውስጥ በስፋት እንደሚፈፀም ጠቁሟል። በአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ አውስትራሊያ እና ኒው ዚላንድ የሚኖሩ ስደተኞች ሳይቀር ሕግን በመተላለፍ ሴት ልጆቻቸውን እንደሚያስገርዙም መረጃው ያሳያል።

መረጃው እንዳመላከተው የሴት ልጅ ግርዛት በብዛት የሚፈጸመው በጨቅላ ህጻናት ላይ ነው። ወደ ትምህርት ቤት ስለማይሄዱ እና ከዕድሜያቸው አንጻር ሪፖርት ማድረግ ስለማይችሉ ተግባሩ እንደተፈጸመባቸው ለማወቅ ከባድ ይሆናል።

የሴት ልጅ ግርዛት አካላዊ እና አዕምሯዊ ጉዳቶችን እንደሚያስከትል ያነሳው ድርጅቱ ይህን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማስቆም ተገቢ ብቻ ሳይሆን ግዴታ መሆኑን አሳስቧል።

እ.አ.አ የካቲት 06 ቀን 2026 የሴት ልጅ ግርዛትን የዜሮ መቻቻል ቀን (FGM) በሚል መሪ ሐሳብ ይከበራል። በዚህም እ.አ.አ በ2030 የሴት ልጅ ግርዛትን ማስቆም ዋና ዓላማ ተደርጎ እየተሠራ ይገኛል። ዕቅዱ ዕውን እንዲሆን የፖለቲካ አመራሩ፣ ማሕበረሰቡ፣ የገንዘብ ምንጮች፣  ምሁራን፣ ወጣቶች እንዲሁም በሴቶች ዙሪያ የሚሠሩ ማናቸውም ተቋማት መተባበር እንደሚገባቸው ተጠቁሟል።

አጋርነትን በማጠናከር፣ ውጤታማ መፍትሄዎችን በማስፋት እና የተቀናጀ እንቅስቃሴን በማጠናከር ግርዛት በሁሉም ቦታ እስኪወገድ እርምጃዎችን ማፋጠን አስፈላጊ ስለመሆኑ ነው የተጠቀሰው።

ኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግርዛትን ለማስቀረት በርካታ የሕግ ማሻሻያዎችን እና ፖሊሲዎችን ካወጡ ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን የዓለም ጠየና ድርጅት ጠቅሷል፡፡ ይህም የሚበረታታ መሆኑን በማንሳት ለተግባራዊነቱ በቁርጠኛነት መሥራት እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

 

( ብርቱካን አትንኩት)

በኲር የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here