የደረጃ እድገት ማስታወቂያ

0
100
  1. ክፍት የስራ መደቡ መጠሪያ የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት የአስ/ጉ/ም/ርዕሰ መምህር
  2. ደረጃ፡ ከፍተኛ መምህር እና በላይ
  3. ደመወዝ፡ የያዘውን እንደያዘ
  4. ስራ ቦታ፡ ደ/ማርቆስ ሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት
  5. ፆታ፡ አይለይም
  6. ብዛት 1
  7. የትምህርት ደረጃ ፡ ሁለተኛ ድግሪ /ማስተር/
  8. የትምህርት ዝግጅት፡ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሚሰጡ የትምህርት ዝግጅቶች በሁለተኛ ድግሪ /ማስተር/ የተመረቀ/ች ወይም በትምህርት ቤት አመራርነት በሁለተኛ ድግሪ የተመረቀ/ች/ እና በመጀመሪያ ድግሪው የማስተማር ሙያ ኮርሶች የወሰደ/ች/ ሆኖ/ና/ የት/ቤት አመራር ስልጠና ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነ/ች/
  9. ተፈላጊ ችሎታ እና የስራ ልምድ፡ በመምህርነት የደረጃ እድገት መሰላል ከፍተኛ መምህር ደርጃ እና በላይ የደረሰ /ች/ሆኖ/ና ከዚህ ውስጥ ቢያንስ ለሁለት አመታት በርዕሰ መምህርነት ወይም በምክትል ርዕሰ መምህርነት፣ በፈረቃ አስተባባሪነት፣ በትምህርት ክፍል ተጠሪነት ወይም በክበባት አስተባባሪነት፣ በተማሪዎች አመራር ኃላፊነት /ጋይዳንስ እና ካውንስለር ወይም በአላማ ፈፃሚ ትምህርት ባለሙያነት በመስራት ላይ ያለ/ች/መሆን ይገባዋል/ታል/፡፡ በትምህርት ባለሙያነት ያሉት መሳተፍ የሚችሉት በመምህርነት ስልጠና የወሰዱ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ተወዳደሪዎች በተወዳደሩበት አመት ያሉ የመጨረሻዎቹ ሶስት ተከታታይ ውጤት ተኮር አፈፃጸም አማካኝ ውጤታቸው አጥጋቢ እና በላይ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ሆኖም በዲሲፕሊን የተቀጣ/ች/ ከሆነ ለውድድር ለመቅረብ ቅጣቱን ያጠናቀቀ መሆን ይገባዋል፡፡
  10. የምዝገባ ቀን ከ15/07/2017 ዓ.ም እስከ 22/07/2017 ዓ.ም ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት
  11. የምዝገባ ቦታ፡ ደ/ማርቆስ መምህራን ኮሌጅ ሲሆን ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት በስልክ ቁጥር 09 20 50 68 87 ዓ.ም ይደውሉ፡፡

የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here