የደብረ ታቦር ከተማ /አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

0
171

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ደብረ ታቦር ከተማ/አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2016 የበጀት ዓመት ለመግዛት
ካቀዳቸው የቢሮ እቃዎች ውስጥ ጠረጴዛ በቁጥር 3፣ ወንበር 12፣ ተሸከሩካሪ ወንበር 3፣
የብረት መደርደሪያ ባለቁልፍ በቁጥር 6፣ ፕሪንተር ቀለም በቁጥር 60፣ የፎቶ ኮፒ ማሽን
ፓውደር ቀለም በቁጥር 50 በ80 ግራም፣ የፕሪንተር ወረቀት 700 ደስታ፣ እስክርቢቶ በፓኮ
50፣ የፋይል ማቀፊያ ኬንት በቁጥር ባለ ብረት 100 እና ባለ ገመድ 100፣ የፕሪንትር ፓውደር
ቀለም በቁጥር 40፣ የወረቀት መምቻ ፓንቸር ትልቁ በቁጥር 10፣ ትንሹ 10 እና ሮሎ ሜትር
ባለ 50 በቁጥር 10፣ ባለ 30 በቁጥር 10 እና ባለ 5 የእጅ ሜትር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ
መግዛት ይፈልጋል:: በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች
መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል::
1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው::
2. ያቀረቡት ዋጋ ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ
መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባችው::
3. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-2 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ
ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
4. የግዥው ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት የሚቻል ሲሆን
የሰነድ መግዣ ዋጋ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ነው::
5. ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ::
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 18,000.00
/አሰራ ስምንት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ (የክፍያ ትዕዛዝ
/ሲ.ፒ/ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ከሥራና ስልጠና
መምሪያ ድጋፍ ማስያዝ ይችላሉ::
7. የጨረታ ሰነድ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ገንዘብ ያዥ
ቢሮ ቁጥ 11/12 ይገኛል::
8. የጨረታ ሳጥኑ መሰረተ ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ይገኛል::
9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ
መብቱ የተጠበቀ ነው::
10. የክልሉን ግዥ መመሪያዎች እስከ ማሻሻያዎች ተግባራዊ የምናደርግ መሆኑን እንገፃለን::
11. ተጫራቾች ኦርጅናል /ዋና/ የጨረታ ሰነዳቸውን በአንድ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ
አለባቸው::
12. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆያል:: ውድድሩ በእያንዳንዱ
ሎት ድምር መሆኑን እገልፃልን:: እያንዳንዱን ሎት ሁሉንም ዝርዝር ያልሞላ ከውድድሩ
ውጭ ይሆናል::
13. ጨረታው በ16ኛ ቀን 4:00 ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው
በተገኙበት ይከፈታል:: ነገ ገን መጨረሻ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን
ይከፈታል:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 00 91 /0058 /058 441 02 03
መደወል ይችላሉ::
የደብረ ታቦር ከተማ /አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here