የደናክል አዘቅት

0
93

የደናክል አዘቅት (ዝቅተኛ ስፍራ) በሰሜን ኢትዮጵያ በአፋር ክልል ነው የሚገኘው፡፡ ስፋቱ በግምት 200 በ 50 ኪሎ ሜትር ወይም 124 በ 31 “ማይል” ተለክቷል፡፡

የደናክል ሸለቆ ወይም አዘቅት የአዋሽ ወንዝ በቀጣናው ደርሶ ሰምጦ ወይም “አፍሬራ”የጨው ንጣፍ መገኛ ሐይቅ ገብቶ የሚጠፋበት  ነው ተብሎ ይታሰባል-  በባለሙያዎች፡፡ የደናክል አዘቅት መገኛው ከባህር ወለል በታች 125 ሜትር ወይም 410 ጫማ ተለክቷል፡፡

የአዘቅቱን ቅድመ አፈጣጠር በተመለከተም የእስያ እና የአፍሪካ አህጉር በመሬት ውስጥ ኃይል ሲናጥ እና የተወሰነ ክፍተት ወይም መራራቅ ፈጥሮ የታችኛው ወለል ቁልቁል በመስመጡ እንደ ሆነ ነው በድረ ገፆች የሰፈረው፡፡

የደናክል አዘቅት እጅግ አስደናቂ የስነ ምድር ገፅታዎችን የያዘ ሦስት ነጥብ ሁለት ሚሊዬን ዓመት ያስቆጠረው ቀጣና ነው፡፡ ከነዚህ መካከል የሰው ልጅ ቀደምት ሦስት ነጥብ ሁለት ሚሊዬን ዓመት ያስቆጠረው ቅሪት  አካል (ሉሲ)፣ የዳሎል ጨዋማ ፍል ውኃ ምንጮች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

የደናክል አዘቅት ወይም ዝቅተኛ ቀጣናን ለመጐብኘት ከትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ በተሽከርካሪ የተወሰነ ርቀትን በአስፋልት፣ ከዚያም አቧራ በሚቦንበት አሽዋማ መንገድ መጓዝ ግድ ይላል፡፡

የደናክል ዝቅተኛ ቀጣናን ለመጐብኘት ከህዳር እስከ የካቲት ያሉት ወራት ይመከራሉ፡፡ አሊያ ግን ሙቀቱ በጣም ስለሚያይል አስቸጋሪ እንደሚሆን ነው ድረ ገፆች ያስነበቡት፡፡

ለዘገባችን በመረጃ ምንጭነት ታይምለስ ኢትዮጵያ፣ ብሪሊያንት ኢትዮጵያ እንዲሁም ጃክኤንድ ጂል ትራቭል ድረገ ፆችን ተጠቅመናል፡፡ (ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዝያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here