የደንዲ ኃይቅ

0
72

የደንዲ ኃይቅ በኦሮሚያ ክልል፣ ምእራብ ሸዋ ከዋና መዲናዋ አዲስ አበባ ደቡብ ምእራብ አቅጣጫ 88 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው የሚገኘው:: በተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ቦሌ በሚወስደው አውራ ጐዳና ወደ ምእራብ አቅንቶ ግንደ በረት ከተማ አቅራቢያ  በተተከለው አቅጣጫ ማመላከቻ መሰረት ተጉዞ ከደንዲ ከተማ በምስራቅ በኩል ጥቂት ኪሎ ሜትር ተጉዞ  መድረስ ይቻላል::

የደንዲ ኃይቅ የክብደት ማንሻ (dumbbele) ወይም ከ “8” ቁጥር ቅርጽ ጋር ይመሳሰላል፤ አጠቃላይ ስፋት ስምንት ኪሎ ሜትር እጥፍ ተለክቷል:: ስፋቱ መካከል ላይ የሚጠብበት ደግሞ 220 ሜትር ብቻ ነው::

ደንዲ ኃይቅ ከከበበው አቀበት በዝናብ ወቅት በሚወርድ ፍሳሽ ይታደሳል መገኛ ከፍታው 2 ሺህ 836 ሜትር ወይም 9 ሺህ 305 “ማይል” ከመሬት ወለል በላይ ተለክቷል::

በኃይቁ ዙሪያ የሚገኘው ሜዳ አረንጓዴ መንጣፍ የለበሰ ነው:: በደንዲ ተራራ ጫፍ ኃይቁን እና ዙሪያውን መመልከት ለጐብኚዎች የሀሴት ምንጭ ነው::

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሚያዝያ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here