የደን ሽያጭ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
80

በሰሜን ጎጃም ዞን በዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር በአብችክሊ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጁፊ በሚባል ቦታ የሚገኘውን በ34 ሄ/ር መሬት ላይ የለማ የባህር ዛፍ ደን የማህበረሰብ ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ማሟላት አለባቸው፡-

  1. ለጨረታ የቀረበውን ደን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በተገለጸው ቦታ ድረስ በመሄድ ጨረታው ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 /ለሃያ/ ቀናት ማየት ይቻላል፡፡
  2. የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሠነድ ጨረታውን ባወጣው መ/ቤት በመገኘት ከዱርቤቴ ከተማ/ገ/ኢ/ል/ትብ/ጽ/ቤት ክፍያውን በመክፈል ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ ብቻ ከፍሎ በሥራ ቀናት መግዛት ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች ሚጫረቱበትን የደን ዓይነት ለመግዛት የሞሉትን ዋጋ አስር መቶ የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ደን ዓይነት መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  4. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን የእያንዳንዱን የደን ዓይነትና መጠን እንዲሁም የሚገዙበትን ዋጋ ከስማቸውና ከአድራሻቸው ጋር በተናጠል በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጎጃም ዞን በዱርቤቴ ከተማ አስተዳደር የማህበረሰብ ደን ጨረታ ተብሎ በጉልህ ከተፃፈበት በኃላ ለዚሁ ተግባር ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር እስከ 20ኛ ቀን 11፡00 በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመቁጠር በ20ኛው ቀን 11፡00 ላይ ጨረታው ይዘጋል፡፡ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ ይካሄዳል፡፡
  6. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 223 04 98 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡
  7. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. በአጣና ወይም በጣውላ ንግድ የተሰማሩ ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ እና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. ደኑን ለግል ፍጆታ ጥቅም ላይ ማዋል የሚፈልጉ መንግስታዊ መ/ቤቶች ከፊል መንግስታዊ ድርጅቶች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ማህበራት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች የደን ውጤቱን የሚገዙበትን ክልል መነሻ በማድረግ በመመሪያው መሰረት በጨረታ የሚካፈሉባቸውን የደን ዓይነቶች እና የዋጋ መጠን ግልጽ በሆነ ጽሑፍ በትክክል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች በሙሉ ወይም በከፊል በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች ከአንድ ክፍልፋይ በታች ሊጫረት አይችልም፡፡
  12. ለጨረታ ሚቀርበው ዋጋ መግለጫ ሥርዝ ድልዝ የሌለበት ሆኖ በተጫራቹ በራሱ ወይም በህጋዊ ወኪሉ አማካኝነት ተሞልቶና ተፈርሞ ማህተም ካለው ተደርጎበት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሥርዝ ድልዝ ካለም ዋጋውን በሞላው ሰው ፓራፍ መደረግ ይኖርበታል፡፡
  13. በጨረታው ተካፋይ የሆነ ተወዳዳሪ የጨረታ ሳጥኑ የመወዳደሪያ ዋጋ የማስገቢያ ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ዋጋውን መለወጥና ማሻሻል ወይም በጨረታው አልካፈልም ማለት አይችልም፡፡ አልካፈልም ብሎ ካወጣም ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች ሌሎችን ተጫራቾች በሠጡት ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
  15. ተጫራቾች አሸናፊ መሆኑ በተገለጸለት እስከ 15 ቀን ባለዉ ጊዜ ዉስጥ የዋጋዉን አስር በመቶ የሥራ አፈፃፀም ዋስትና በማስያዝ እና የአሸነፈበትን የደኑን ጠቅላላ ዋጋ በመክፈል ቀርቦ ዉሉን ይፈርማል፡፡
  16. የዉል ግዴታዉን ያልተወጣ ተጫራች ያሥያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ይወረስበታል፡፡ ተጨማሪ ጉዳት ካደረሰም በህግ ሊጠየቅ ይችላል፡፡
  17. የጨረታ አሸናፊዉ የሮያሊቲ ክፍያ የደን ልማት አገልገሎት የሚውል ስምንት በመቶ እና የደን ዉጤቱን ከቦታ ቦታ ለማቀሳቀስ ደግሞ አምስት በመቶ በድምሩ አስራ ሶስት በመቶ ይከፍላል፡፡

የአብችክሊ ዙሪያ ቀበሌ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here