የዳግማዊ ምኒልክ አጎት ራስ ዳርጌ ሣህለ ሥላሴ በተወለዱ በ70 ዓመታቸው አርፈው በደብረ ሊባኖስ የተቀበሩት በያዝነው ሳምንት መጋቢት 15 ቀን 1892 ዓ.ም ላይ ነበር።
በተመሳሳይ የቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ አባት፣ ልዑል ራስ መኮንን ቁልቢ ላይ አርፈው ቀብራቸው በሐረር ከተማ መጋቢት 12 ቀን 1898 ዓ.ም ተፈፅሟል።
በተጨማሪም መጋቢት 10 ቀን 1936 ዓ.ም ላይ የስመ ጥሩው አርበኛ ደጃዝማች ዑመር ሰመተር ዜና እረፍት የተሰማው፡፡
ምንጭ፤ ታሪክ ማስታወሻ
(መሰረት ቸኮል)
በኲር መጋቢት 9 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም