የዳኝነት ነጻነትን ማክበር ፍትሕ እንዲረጋገጥ ሚናው የጎላ ነው

0
63

የዳኝነት ነጻነት በማክበር  እና  የዳኞችን ከለላ ጠንካራ ማድረግ ገለልተኛ ፍርድ ቤቶችን በመገንባት ሂደት ሚናው የጎላ እንደሚኾን ተገለፀ፡፡

“የፍርድ ቤቶች ነጻነት እና ገለልተኛነት ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ያለው ፋይዳ” በሚል መሪ መልዕክት በሰብዓዊ መብቶች አከባበር ዙሪያ ለዳኞች እና ለፍትሕ አካላት ሥልጠና ተሠጥቷል፡፡

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ  ዓለምአንተ አግደው ነጻ እና ገለልተኛ ፍርድ ቤቶችን  ማቋቋም ፣ የዳኝነት ነጻነት እና የዳኞች ከለላ ማድረግ ለዳኞች ጥቅም ተብለው የሚወጡ ሕጎች አለመሆናቸውን ገልፀው፤ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ዳኞች በሕግ ላይ በመመስረት እና ለሕሊናቸው ብቻ በመታመን ከፍርሃት እና ካልተገባ ጫና ነጻ ኾነው ፍትሕን እንዲያረጋግጡ ለማስቻል ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ የዳኝነት ነጻነት መከበር በሦስቱ የመንግሥት አካላት መካከል ያለውን የቁጥጥር እና ክትትል ሥርዓት በማጠናከር የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን ያደርጋል  ይህም ዜጎች በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ እምነት እንዲያሳድሩ የሚያስችል  ተግባር  ነው  ብለዋል፡፡

የሕግ የበላይነትን እና የሰብዓዊ መብትን ለማክበር መንግሥታት ነጻ የዳኝነት አካልን ተቋማዊ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡

ኢሰመኮም የዳኝነት ነጻነትን ለማምጣት  የሚረዱ አሠራሮችን እውቅና ይሰጣል ድጋፍም ያደርጋል ብለዋል፡፡

(ማራኪ ሰውነት)

በኲር የግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here