የጄኔራሉ ስቅላት

0
205

የታህሳስ ግርግር በመባል በታሪክ መዝገብ የሚታወቅ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ሃገራችን አስተናግዳለች።

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን በግንባር ቀደምነት ያካሄዱት የክብር ዘበኛ አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል መንግሥቱ ነዋይ እና ግርማሜ ነዋይ ናቸው።

የመፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎቹ “የኢትዮጵያን ማኅበራዊ እና ብሔራዊ የእድገት እርምጃ ጥቂት ራስ ወዳድ ግለሰቦች ወደ ኋላ አስቀርተውታል፤ በአጠቃላይ አገዛዙ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል አየጎዳ ነው፤ የህዝቡ ቁጭት ለዚህ አነሳስቶታል” የሚሉና ሌሎችም መልዕክቶች በማኒፌስቶነት በራዲዮ እንዲሰራጩ ሆኖ ነበር። የመፈንቅለ መንግስት ሙከራው ባለመሳካቱም፤ ጃንሆይ ለጉብኝት ከሄዱበት ላቲን አሜሪካ ወዲያው ተመለሱ፤ በጀነራሎቹ ላይም ክስ ተመሰረተ።

ጀኔራል መንግሥቱ ንዋይ በተከሰሱበት የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ወንጀል በስቅላት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ወሰነ። በዚህም መሠረት መጋቢት 21 ቀን 1953 ዓ.ም በስቅላት ተቀጡ።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ታሪክ፡ ከ1847-1983(ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ)

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here