ታላቁ የስፖርት ሰው በሀገራችን የእግር ኳስ ጫማ ተጫምተው የተጫወቱ የመጀመሪያው የእግር ኳስ ተጫዋች ናቸው፡፡ በቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ለ23 ዓመታት ያህል በታማኝነት ተጫውተው አልፈዋል፡፡
የአፍሪካ እግር ኳስ ማህበርን የመሰረቱ፣ በፕሬዝዳንትነትም ለ15 ዓመታት ያገለገሉ ናቸው፡፡ በአሰልጣኝነት ዘመናቸው ደግሞ ብቸኛውን የመድረኩን ዋንጫ አሳክተዋል፡፡
በፊፋ የካፍ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል፣ የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል በመሆን አገልግለዋል:: በእነዚህ የኃላፊነት ዘመናቸውም በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የአፓርታይድ ሥርዓት በመዋጋት ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው::
የሞሮኮ እግር ኳስ ፌደሬሽን በካዛብላንካ የሚገኘውን ስቴዲየም በእርሳቸው ስም ስያሜ ሰጥቶታል፡፡ በካፍ (CAF) በየዓመቱ በሚዘጋጁ የኮከቦች ሽልማት ዘርፍ ላይ በይድነቃቸው ተሰማ ስም ለአፍሪካ እግር ኳስ እድገት አስተዋጽኦ ላበረከቱት ግለሰቦች ሽልማት መስጠት ተጀምሯል፡፡
ዝርዝሩን ከስፖርት አምዳችን ያንብቡ!