የጉልበት መገጣጠሚያ ህመምን የሚያስታግሰው

0
274

የጉልበት አጥንትን የሚያያይዘው ጠንካራ እና ለስላሳ የጅማት ስብስስ (ካርቲሌጅ) መስነፍ እና የማበጥ ህመም “ኦስቲዮ አርትራይተስ”ን በማስታገስ እየባሰ እንዳይሄድ  የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ማዘውተር ውጤታማ ስልት መሆኑን ሳይቴክ ዴይሊ ድረ ገጽ ከሳምንት በፊት አስነብቧል::

“ቢኤምጂ” የተሰኘ የአጥኚዎች ቡድን የምርምር ውጤቱን ለህትመት ባበቃው መድሄት በእግር መጓዝ፣ ዋና፣ ብስክሌት መንዳት የመሳሰሉት በጉልበት ህመም ከእንቅስቃሴ መገታትን እንደሚያሻሽሉ አስፍሯል:: አብዛኛዎቹ የህመሙ ተጠቂዎችም እድሜያቸው ከ45 ዓመት  በላይ የሆናቸው ናቸው::

“ኦስቲዮ አርትራይተስ” ወይም የጉልበት ማያያዣ (ካርቲሌጅ) ህመምን ለማሻል በሀኪም ከሚሰጠው መድሃኒት በተጨማሪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፈውስን የሚያፋጥን ስልት ሆኗል:: ከዚሁ ጋር ተያይዞ የትኞቹ እንቅስቃሴዎች ተመራጭ እንደ ሆኑም ለይተው ውጤታማነታቸውን እና ደህንነት ላይ የሚኖራቸውን ተፅዕኖም ገምግመዋል::

ጥናት እና ምርምሩ ከ1990 እስከ 2024 ባሉት ዓመታት 15,684 ተሳታፊዎችን አካቷል:: የውጤት መለኪያዎቹም- የህመም መቀነስ፣ የመንቀሳቀስ ዓቅም መሻሻልን መሰረት አድርገው ለወራት በተደረገ ክትትል የተገኘ መሆኑን ነው ጽሁፉ ያመላከተው::

በናሙና ጥናትና ምርምሩ የተሳታፊዎች ብዛት፣ የጊዜ መርዘም እና ማጠር በውጤቱ ላይ ተፅዕኖ ማሳረፉን አስተውለዋል- አጥኚዎቹ:: ይህም የጊዜ መርዘምና ማጠሩ ውጤቱን የተለያየ እንዳደረገው ለማረጋገጥ አስችሏቸዋል::

የሆነው ሆኖ ከተሰበሰበው የመረጃ ትንተና እና ከአጠቃላይ ሂደቱ ተጨምቆ የወጣው ውጤት ማጠቃለያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የጉልበት መንቀሳቀስ ዓቅምን ለማሻሻል እና ህመምን ለመቀነስ ሁነኛ አማራጭ መሆኑን ነው ያሰመሩበት- ተመራማሪዎቹ::

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here