የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የ2016 በጀት ዓመት ሂሳብ በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡-
- ጽ/ቤቱን /ድርጅቱን/ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ደረጃ ያለው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የሙያና የንግድ ፈቃዳቸውን ያደሰ፡፡
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጭው አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጲያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማሕበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የበጀት ዓመቶች ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ በሰጠው ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያከናውኑት ተግባር ከድርጅቱ ጋር ዝርዝር ውል ለመፈራረም ፈቃደኛ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ስለ መልካም ሥራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት የሂሳብ ምርመራ /ኦዲት/ ካደረጉባቸው ድርጅቶች የተፃፈላቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የንግድ ሥራ ፈቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት /ተመዝጋቢ ከሆነ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት /ቲን/ እና ሌሎች ለጨረታው የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሂሳብ ምርመራ /ኦዲት/ ጎንደር ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ከ03/06/2017 ዓ.ም እስከ 17/06/2017 ዓ.ም በሥራ ሰዓት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን /ታክስን ጨምሮ/ በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ቢሮ ቁጥር 14 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የበጀት አመቱን ኦዲት ሥራ የኦዲት ሥራው የሚከናወንበትና የሥራ ዝርዝር እና በመጨረሻ የሚያቀርቡት የኦዲት ሪፖርት ይዘት እንዲሁም የሚወሰድባቸውን ጊዜ በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር /ማስኬጃ ውል/ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን 17/06/2017 ዓ.ም ጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 14 ይከፈታል፡፡
- 15ኛው ቀን በዓል /የእረፍት ቀን/ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ በአገር አቀፍ በዓል ምክንያት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 የሥራ ቀናት ነው፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ 058 111 04 59 /058 211 33 16 በመደወል በማነጋገር ይችላሉ፡፡
ፋክስ ቁጥር 058 111 43 72
የጎንደር ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት