የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
92

በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ የሐይቅ አጠቃለይ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ቆርቆሮ በቆርቆሮ የሆነ መሰብሰቢያ አዳራሽ ት/ቤቱ የግንባታ እቃዎችን እራሱ አቅርቦና የእጅ /የሙያ/ ዋጋ ከፍሎ ለማሰራት ይፈልጋል። ሎት 1. የግንባታ እቃዎች ግዥ እና ሎት 2.የእጅ /የሙያ/ ዋጋ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሎት /በጥቅል ዋጋ/ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶች የሚያሟሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው።
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑና እነዚህን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ለሎት 2 ተቋራጮች ደረጃቸው 8 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሆነው ለዘመኑ የታደሰ የሙያ ፈቃድ ያለቸውና የመልካም ስራ አፈጻፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ያሸነፈው ተጫራች ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ በትም/ቤቱ ስም አስይዞ በፍትህ ጽ/ቤት በኩል ከት/ት ቤቱ ጋር ውል ይፈጽማል።
  5. የጨረታ ሰነድ መግዥያ ጊዜ፡- ለሎት 1 ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና በጨረታ መክፈቻ ቀን እስከ 4፡00 ድረስ እንድሁም ለሎት ደግሞ ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት እና በጨረታ መክፈቻ ቀን እስከ 4፡00 ድረስ ሲሆን አመልካቾች ለሐይቅ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ2 በመቶ ሲሆን የዋስትናውን አይነት በሲፒኦ፣በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ሆኖ ለሐይቅ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ተብሎ ከሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች መረጃቸውንና የዋጋ ማቅረቢያቸውን በጥንቃቄ በታሸጉ በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት ለሎት 1 ማሳታወቂያው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት 01/07/ 2017 እስከ 16/07/2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ሲሆን ለሎት 2 ደግሞ ማሳታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት 01/07/ 2017 እስከ 22/07/ 2017 ዓ.ም 4፡00  ድረስ ሐይቅ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  8. የጨረታ መክፈቻ ቀን ሎት 1 ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን በ16/07/2017 ሎት 2 ደግሞ ማስታወቂያው ከወጣበት በ22ኛው ቀን በ22/07/2017 ሆኖ በነዚሁ ቀናት 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀናት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ /ባይገኙም ይከፈታል/ የመክፈቻ ቀኖቹ የስራ ቀን ካልሆኑ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. በሎት 1 አሸናፊ የሆነው ድርጅት በውሉ መሰረት እቃዎቹን በራሱ ወጭ አጓጉዞ ለትምህርት ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
  10. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ በማንኛውም ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ካለም ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  11. የክልሉ ግዥ መመሪያ ከነማሻሻያው ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
  12. ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በጨረታው የሚሳተፍ ማንኛውም አካል በስ.ቁ 0332220220 ደውሎ መረጃ መጠየቅ ይችላል፡፡

የሐይቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here