በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በሰሩ ለሚገኘው ለጃ/ወ/ት/ጽ/ቤት በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የበጀት በዋሰል ቀበሌ ዋሰል 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚያሰራው የአስተዳደር ቢሮ በር በተቋሙ የሚቀርብ ሲሆን የበር መግጠም እና ሌሎች ስራዎችን እና አቅርቦቶች በተቋራጩ የሚሸፈን ሆኖ ግንባታውን በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።
- ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የህንጻ ግንባታ ስራ ተቋራጭ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው ፡፡
- ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ በህንጻ ግንባታ ስራ ተቋራጭ የታደሰ ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርትፍኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የማረጋገጫ ሰርትፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃወች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግንባታ አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 / አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1በመቶ ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ -1 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ከ01/07/2017 ዓ/ም እስከ 21/07/2016 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከ01/07/2017 ዓ.ም እስከ 21/07/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡ እንዲሁም ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ለ40 ቀን ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 22/07/2017 ዓ/ም 8፡15 ታሽጎ 8፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታን ከመክፈት አያስተጓጉለውም፡፡
- ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ወድቅ ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 0582940023 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት