የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
67

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ በመደበኛ እና ፕሮጀክት በጀት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ የደንብ ልብስ ግዥ ፣የመኪና ጎማ ግዥ ፣የጽ/መሳሪያ ግዥ እና የመነፀር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በአብክመ መሬት ቢሮ ቁጥር 0-18 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽ) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. አሸናፊ ድርጅት የሚለየው የተጠቀሰውን ዝርዝር መግለጫ ያሟላ ሆኖ በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ሞልቶ ያቀረበ ነው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ደረሰኙን ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች ዋናውን ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዱ በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በአብክመ መሬት ቢሮ ቁጥር 0-18 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ ሰኔ 03 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ መሬት ቢሮ ቁጥር 0-18 ሰኔ 03 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሸጐ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊው ድርጅት ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እቃውን ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ መሬት ቢሮ ቁጥር 0-18 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 71 31 ወይም 058 226 55 06 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአብክመ  መሬት ቢሮ

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here