የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

0
30

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት የመኪና ጎማ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ማንኛዉም ተጫራች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪው ድርጅት ሥም፣ አድራሻ የሚመለከተው ወይም ህጋዊ ወኪል የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በጨረታው የተሳተፈ ማንኛውም ድርጅት ዋጋ ካቀረበ በኋላ ዋጋውን መለወጥና ማሻሻል ወይም በጨረታው አልሳተፍም ቢል ያስያዘውን የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ተመላሽ አይሆንም፡፡
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  5. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከአማራ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መዉሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡበት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተመሠከረለት Cash Payment order (ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት አስገዳጅ የሆነ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሞዴል 85 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  8. ተወዳዳሪዎች ከተሸነፋ ያስያዙት (ቢድ ቦንድ) እንዲለቀቅ በጸሁፍ ሲያሣውቁ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ ስለ ትክክለኛ ሥራ አፈጻጸም ዋስትና (Performance Bond) ያሸነፋበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ አሸናፊነቱ ከተገለጸለት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ በሚቀጥለው 10 ተከታታይ ቀን  (በሲፒኦ) ወይም በጥሬ  ገንዘብ በማስያዝ ውል ይፈጽማል፤ ዉል ካልፈጸመ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በገንዘብ ቢሮ እገዳ ያልተደረገባቸው መሆን አለባቸው፡፡
  11. በጨረታው ለመሣተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  12. የጨረታ ማስከበሪያዉ ጨረታዉ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ካለፈ በኃላ ለ20 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
  13. ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ድረስ የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአማራ ክልል ምክር ቤት ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 40 በተዘጋጀዉ ሳጥን ገቢ ማድረግ አለባቸዉ፤ በዚሁ እለት 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል፤ የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  14. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡
  15. ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊው ተለይቶ ውል ከያዘበት ቀን ጀምሮ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  16. መ/ቤቱ የግዥዉን 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  17. በዋጋ መሙያዉ ላይ ሥርዝ ድልዝ ያለበት ከሆነ ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡
  18. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  19. ሌሎች በዚህ መመሪያ ያለተገለፁ በጨረታ ሰነዱ እና በመንግስት ግዥ አፈፃፀም መመሪያ ተገዥ ይሆናሉ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፖስታ ሣጥን ቁጥር 1324 በመላክ ወይም ስልክ ቁጥር 058 226 21 51 /058 222 14 38 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here