የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
89

በሰሜን ጎንደር ዞን በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት አመት በUNDP በጀት በሰሩ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. ለጃ/ወ/ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት 1ኛ. በመ/ብርሃን ከተማ የከነማ ፋርማሲ ግንባታ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ 2ኛ. በመ/ብርሃን ከተማ የጤና መድህን ቢሮ ግንባታ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ 3ኛ. የዋሰል ጤና ጣቢያ እድሳት በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ሎት2∙ /ጃ/ወ/ት/ት ጽ/ቤት 1ኛ. በመ/ብርሃን ከተማ ቀበሌ 02 የመ/ብርሃን 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ባለ 1 ብሎክ አራት መማሪያ ክፍል ያለው ግንባታ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፣ 2ኛ. በአጥገባ ቀበሌ ጭሮለባ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አንድ የወንዶች መፀዳጃ ቤት አንድ የሴቶች መፀዳጃ ቤት ከዚህ በፊት ተጀምሮ ተቋርጦ የነበረውን ግንባታ በጥገና መልክ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ሎት 3. የጃ/ወ/ፖሊስ ጽ/ቤት በመ/ብርሃን ከተማ ቀበሌ 01 የሚገኘውን ፖሊስ ጣቢያ በድንጋይ ግንብ አጥር በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ የህንጻ ግንባታ ስራ ተቋራጭ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  2. ደረጃ 7 እና ከዛ በላይ በህንጻ ግንባታ ስራ ተቋራጭ የታደሰ ሙያ የብቃት ማረጋገጫ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. የቲን ነምበር ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት /ተመዝጋቢዎች የተጨማሪ ሴት ታክስ /ቫት/ የምዝገባ ሰርፍትኬት ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. በእያንዳንዱ ሎት የግንባታ አይነትና ዝርዝር መገለጫ /ስፔስፍኬሽን /ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 50/ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1በመቶ በእያንዳንዱ ሎት ከሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ አስበው በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመ/ሂ-1 አንድ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ከ15/07/2017 ዓ/ም እስከ 05/08/2017 ዓ/ም ድረስ ይውላል፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር 10 ጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ቀናት ከ15/07/2017 ዓ.ም ዓ.ም እስከ 05/08/2017 ዓ.ም ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡እንዲሁም ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ለ40 ቀን ይሆናል ፡፡
  11. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጃ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ውስጥ  ቢሮ ቁጥር 10 በቀን 06/08/2017 ዓ/ም 8፡15 ታሽጎ 8፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ይከፈታል ፡፡
  12. ጨረታውን የምናወዳድረው በጠቅላላ ድምር /በሎት/ ድምር ይሆናል፡፡
  13. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዲኖረው አይፈቀድም ፡፡
  14. ተጫራቾች ከሚሞሉት ሰነድና ፖስታ ላይ የድርጅታቸውን ህጋዊ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.10 በአካል በመገኘት ወይም በስቁ. 0582940023 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

በጃናሞራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here