የግብጽ ፒራሚዶች

0
22

ልጆች እንዴት ሰነበታችሁ? ትምህርት እንዴት ነው? ወቅቱ የተለያዩ ወረርሽኞች የተከሰቱበት በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይጠበቅባችኋል፤

ልጆች በአፍሪካ የሚገኘውን ከዓለም ድንቅ ጥንታዊ ቅርሶች መካከል አንዱ የሆነውን የጊዛ ፒራሚዶች (የግብጽ ፒራሚዶችን) እናስተዋውቃችሁ፡፡

የግብጽ ፒራሚዶች (የጊዛ ፒራሚዶች) በውስጣቸው ያሉ ምስጢራት፣ አካላዊ ቅርፀ ሁኔታቸው እና አሰራራቸው በቅርብ በወጡ አንዳንድ ጥቂት እውነታዎችና ድንቅ ሣይንሳዊ ግኝቶች ራሳቸውን ከመግለጣቸው በፊት፤ በአፈታሪኮች እና ተረቶች ምንነታቸው ተደብቆ፣ ተጠቅልሎ እና ተሸፍኖ የነበረ ታላቅ ምሥጢራዊ ፒራሚዶች ናቸው።

በግብፅ ከ130 በላይ ፒራሚዶች ይገኛሉ። የገነቧቸውም ሙታንን በዚያ ለማኖር እና  ለነርሱ ከሞት በኋላ ላለው ህይወታቸው የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ እንዲይዝላቸው በሚል ነው።

ብዙዎቹ ፒራሚዶች የሚገነቡትም ለፈረዖኖች (ንጉሦች) እና ለቤተሰቦቻቸው መቃብሮች እንዲሆኑ ነው። ፒራሚዶች የሚነደፉትም ዋናው መግቢያቸውን በሰሜን በኩል እንዲሆን ተደርጎ ነው።

ፒራሚዶች የሚገነቡት በገበሬዎች እና በጉልበት ሰራተኞች (በባሪያዎች) እንደነበር ብሪታኒካ በመረጃው ያሳያል። 20 ዓመታትን በወሰደው ግንባታ ከ100 በላይ ሰዎች እና ዝሆንን ጨምሮ የተለያዩ እንስሳት መሳተፋቸውን ጠቅሷል፡፡

ፒራሚዶቹ የተገነቡባቸው አብዛኞቹ ድንጋዮች እስከ ሁለት ሺህ 370 ኪሎ ግራም ክብደት ድረስ ሲመዝኑ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ እስከ 72 ሺህ 575 ኪሎ ግራም ድረስ የሚመዝኑ ትልልቅ ድንጋዮች ናቸው።

ድንጋዮቹንም ለማንቀሳቀስ ሰራተኞቹ ይጠቀሙት የነበረው ዘዴ (technique) መውጫ መውረጃ ደረጃዎችን (ramps) በመሥራት ነበር። በቀላሉ እንዲንሸራተትላቸውም በጭቃ ወለሉን ይለቀልቁታል።

ፒራሚዶቹ ቁመታቸው 146 ነጥብ አምስት ሜትር (481 ጫማ) ሲሆን በታሪክ ረዥሙ “ሰው ሠራሽ” መዋቅር በመባል፤ ምድር ላይ ካሉ ድንቃድንቆች አንዱ በመሆን  ከ3,800 ዓመታት በላይ ምድራችን ላይ ቆይተዋል።

ተረት

ቀበሮዋ እና አያ ጅቦ

አንዲት ሁለት ግልገሎች የነበሯት ቀበሮ ነበረች:: አንደኛውን ልጇን ወይና ብላ ሰየመችው (ይህም ማለት እምብዛም ያልፈካና እምብዛም ያልጠቆረ ማለት ነው):: የሌላኛው ግልገል ስም ጌላ ነበር:: ቀበሮዋም ምግብ ፍለጋ ስትሄድ  ግልገሎቿን ዘግታባቸው ትሄድ  ነበር:: ቀበሮዋም ወደቤቷ ስትመለስ እንዲህ ትላለች፤

“አንድ ወይና አንድ ጌላ  በሩን ክፈቱልኝ”

ታዲያ አንድ ቀን ቀበሮዋ ልጆቿን ስትጣራ አያ ጅቦ ይሰማና፤ ቀበሮዋ ወደ አደን ስትሄድ እናታቸውን አስመስሎ ጠራቸው:: ግልገሎቹ ግን ድምፁ ስለተለየባቸው ተጠራጠሩ:: በዚህ ጊዜ ጅቡ ድምፁን የበለጠ አቅጥኖ የጥሪ ቃላቱን ሲደግም እናታቸው መስላቸው በሩን ሲከፍቱ ጅቡ በላቸው::

ቀበሮዋም ወደቤቷ ተመልሳ በተለመደ ድምጿ ልጆቿን ብትጣራ መልስ አጣች::  ወደ ቤቱ ውስጥም ዘላ ስትገባ ግልገሎቹ በጅቡ እንደተበሉ አወቀች:: በሚቀጥለው ቀን ታዲያ ቀበሮዋ ጉድጓድ አዘጋጅታ ጉድጓዱን በፍየል ቆዳ ከሸፈነችው  በኋላ ጅቡን አንዲት በግ ከእርሷ ጋር  ተካፍሎ እንዲበላ ጋበዘችው:: “ና ብላ” ብላ ስትጠራው ጅቡ በመጣ ጊዜ “የፍየሉ ቆዳ ላይ ተቀመጥ” አለችው:: ነገር ግን ጅቡ የፍየሉ ቆዳ ወደ ጉድጓዱ ውስጥ በመጠኑ ጎድጎድ ማለቱን አየ:: ቀበሮዋ ግን “ኧረ ምንም አይደል! እዚያ ተቀመጥ” ስትለው አያ ጅቦ ቆዳው ላይ ሲቀመጥ ወደ ጉድጓዱ ውስጥ ወደቀ፡፡ ልጆች የማታውቋቸውን ሰዎች ስትቀርቡ መጠንቀቅ እንዳለባችሁ ከተረቱ ትማራላችሁ፡፡

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ተረቶች

ሞክሩ

  1. አወራለሁ ግን አልሰማም? ሬዲዮ
  2. በኢትዮጵያ ትልቁ ተፈጥሯዊ ሐይቅ ማን ይባላል? ጣና
  3. ጥርሶች አሉኝ መብላት ግን አልችልም፤ እኔ ማን ነኝ? ማበጠሪያ

ነገር በምሳሌ

 

  • ሁሉ ሆነ ቃልቻ ማን ይሸከም ስልቻ፤ ሁሉም እኔ ነኝ አዋቂ ካለ ማን ሠርቶ ይብላ፡፡
  • ለማያውቅ ፎገራ ዱሩ ነው- ፎገራ ለጥ ያለ ሜዳማና ምንም ዛፍ የሚባል የሌለበት ቦታ ነው፤ ለማያውቀው ሰው ግን በደን የተሸፈነ ጫካ ያኽል ያደናግራል፡፡
  • የዓባይን ልጅ ውሃ ጠማው፤ እያለው እንደሌለው የሚቸገር ማለት ነው::

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here