የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ ማስታወቂያ

0
23

ለጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በ2550 ባለአክሲዮኖች በብር 54,110,000 መነሻ   ካፒታል በመያዝ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ፈቃድ ስለመስጠትና ስለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 626/2001 (እንደተሻሻለው) መሰረት እ.ኤ.አ በ03/06/2022 እውቅና በማግኘት ወደ ሥራ ገብቷል፤ በመሆኑም 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 በሙሉ ዓለም የባሕል ማዕከል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጉባኤውን ያካሃዳል፤ ስለሆነም ሁሉም ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በጉባዔው እንድትገኙ ጥሪ እናስተላለፋለን፡፡

የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. የጉባኤውን አጀንዳዎች ማጽደቅ፡፡
  2. አዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል፡፡
  3. በነባር በባለአክሲዮኖች የተገዙ ተጨማሪ አክሲዮኖችን መቀበልና ማጽደቅ፡፡
  4. በባለአክሲዮኖች የተደረገ የአክሲዮን ዝውውርን ማጽደቅ፡፡
  5. የዳይሬክተሮች ቦርድ የ2024/25 በጀት ዓመት ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፡፡
  6. የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፡፡
  7. በ2024/25 በጀት ዓመት በተገኘው ትርፍ ክፍፍል ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፍ፡፡
  8. በ2024/25 ከተገኘዉ ትርፍ ላይ ለሥራ አመራር ቦርድ ክፍያ ተወያይቶ መወሰን፡፡
  9. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፡፡

የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  1. በንግድ ህጉ አንቀጽ 255 እና አንቀጽ 400 መሰረት የአክሲዮን ማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ላይ ተወያይቶ ማሻሻል፡፡
  2. የጉባኤውን ቃለ-ጉባኤ ማጽደቅ፡፡

ማሳሰቢያ፡- በጉባዔው ለመሳተፍ ስትመጡ የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ እንድትይዙ እና በጉባዔው መገኘት ለማትችሉ ባለአክሲዮኖች ከጉባዔው 3 ቀናት በፊት የዘመኑ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ባሕር ዳር ከተማ አጼ ሰርፀ ድንግል ት/ቤት ጀርባ በሚገኘው በዋና መስሪያ ቤቱ ጽ/ቤት ወይም በተቋሙ ቅርንጫፎች በአካል በመገኘት እንድትወክሉ ወይም ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ የተሰጠ የውክልና ሰነድ በመያዝ በስብሰባው ላይ እንድተገኙ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

የጣና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here