በአፈ /ከሳሽ ወለላው ሰፈነ እና በአፈ/ ተከሳሽ ጋሻው እሸቱ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ ፤ ባ/ዳር ከተማ ዳግማዊ ምኒሊክ ክ/ከተ/ ሠላም ቀበሌ ፤በወለላው ሰፈነ ስም የተመዘገበ በሰሜን፣ በደቡብ እና በምዕራብ መኖሪያ ቤት ፣ በምስራቅ መንገድ 1010 ካ.ሜ የሆነ በ4/ቁ 6434 ካርታ ቁጥር፣ ደ/ም/ክ/ከ/1594/2013፣ G+2 መኖሪያ ቤት በጨረታ መነሻ ዋጋ 6‚751‚964 /ስድስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ አንድ ሽ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አራት/ ብር ስለሚሸጥ ፤የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ ፤ጥር 24/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ በግልፅ ጨረታ ይሸጣል፡፡ መጫረት የምትፈልጉ ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በሰዓቱ በቦታው በመገኘት ተመዝግባችሁ መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈበትን ¼ ኛውን በሞ/85 ወዲያውኑ ማስያዝ የሚጠበቅበት መሆኑን ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡
የባሕር ዳርና አካ/ከ/ፍ/ቤት