የጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ደ/ማ/ዲ /ግጨ001/2016
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደ/ማርቆስ ዲስትሪክት ከዚህ በታች የተገለፁትን የከባድ መኪና መለዋወጫ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት | የዕቃው ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ | የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
1 | የተለያዩ አይነት የከባድ መኪና መለዋወጫ ግዥ | 10,000.00 | ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡0 | ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
2 | የተለያዩ አይነት የዘይት እና ግሪስ ግዥ | 10,000.00 | ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 | ሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ያላቸው የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ያላው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ከሰኔ 03/2016 ዓ.ም ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ደ/ማ/ዲስትሪክት በሚገኘው ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት እቦሳ የገብያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 10 ስልክ ቁጥር 058 178 46 33 /058 178 12 02 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ‹‹Ethiopia Electric Utilty›› የሚል የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ሰኔ 13/2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደ/ማርቆስ ዲስትሪክት