የጨረታ ማስታወቂያ

0
126

የጨረታ ቁጥር EEU-AREU/BDD/001/2017

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባሕር ዳር ዲስትሪክት በመሸንቲ ከተማ የቤት ማህበር ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ተ.ቁ የስራው አይነት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ሲፒኦ የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት
1 የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ 10,000.00 ሀምሌ 22ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሀምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30
  1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ በፌዴራል መንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ያልታገደ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ከሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 408 በመምጣት የማይመለስ 300.00 /ሶለት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. አድራሻ፡- ባሕር ዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባሕር ዳር ዲስትሪክት 3ኛ ፎቅ ባሕር ዳር ዲስትሪክት ግዥ አቅርቦት ዌርሃውስ እና ፋሲሊቲስ ቢሮ ቁጥር 303 ስልክ ቁጥር 058 320 51 12/ 058 320 69 99 በመደወል መረጃ ማግኝት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና “ETHOPIAN ELECTRIC UILITY BAHIR DAR D/SIRIGI” በሚል መሆን ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ  ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡

ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባሕር ዳር ዲስትሪክት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here