የአብክመ ፍትህ ቢሮ ለ2017 ዓ.ም ለዐቃቢያን ሕግ ሰርቪስ አገልግሎት የኪራይ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የመኪና ኢንሹራንስ፣ የቢሮ ፅዳትና ውበት፣ የመኪና ጥገና ጋራዥ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ሎት 1. ለዐቃቢያን ሕግ ሰርቪስ አገልግሎት ኪራይ፣ ሎት 2. የመኪና መለዋወጫ ፣ ሎት .3 የመኪና ኢንሹራንስ፣ ሎት 4. የቢሮ ፅዳትና ውበት ፣ ሎት 5. የመኪና ጥገና ጋራዥ ግዥ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከ200,000.00 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከተ.ቁ.1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው ነገር ግን ከላይ ከ1-2 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ 50.00 /ሀምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል አብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ የዕቃውን ወይም የአገልግሎቱን ዋጋ ለዐቃቢያን ሕግ ሰርቪስ አገልግሎት ኪራይ ሎት 1. 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/፣ የመኪና መለዋወጫ ሎት 2. 50,000.00/ሀምሳ ሺህ ብር/፣ ለመኪና ኢንሹራንስ ሎት3. 5,000 /አምስት ሽህ ብር/፣ ለቢሮ ፅዳትና ውበት ሎት4. 3,000 /ሦስት ሽህብር/፣ ለመኪና ጥገና ጋራዥ ግዥ ሎት5. 20,000/ሃያ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሥሪያ ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገፅ ማህተማቸውንና ፊርማቸውን በማስቀመጥ ፖስታውን በሚገባ በማሸግ ለአብክመ ፍትህ ቢሮ ግዥ ባለሙያዎች ቢሮ ቁጥር 04 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ29/11 /2016 ዓ.ም እስከ 16ተኛው ቀን 13/12/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ፍትህ ቢሮ መሥሪያ ቤት ቢሮ ቁ. 04 በ16ተኛው ቀን 14/12/2016 ዓ.ም በ3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በመሥሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ ፍትህ ቢሮ