የጨረታ ማስታወቂያ

0
136
የጨረታየጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አብክመ/የወ/ኩ/ም/አገ/ብግጨ/02/2017
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት መገልገያ የሚሆን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ግልጽ ጨረታ በሎት ወይም በተናጠል አወዳድሮ  ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ተጠሪ መሥሪያ ቤቱ  የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል::
  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው::
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው::
  3. የግዥው መጠን 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል::
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 406 ማግኘት ይቻላል::
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች /ሎቶች/ አንድ በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት  የተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው::
  8. ለተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ተጫራቾች ከአንድ ቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥና ንብ/አስተ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 406 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 403 ጨረታው በኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል::
  10. መሥረያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 31 68 ፋክስ 058 320 11 83 ፖ.ሳ.ቁ 965 በመደወል ማግኘት ይቻላል::
የአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here