በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረ/ቤቶች ኮሚሽን ለ2017 በጀት አመት የተለያዪ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣የፅህፈት መሳሪያዎች ፣ፈርኒቸር እና የተለያዪ ተሸከርካሪ ዲኮር እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅርብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚሰሩ ስራዎች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር / በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 ማግኘት ይቻላል።
- የጨረታ ሰነድ የመሸጫ ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ በግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 226 63 67 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 71 04 ወይም 058 226 6035 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ ባህር ዳር ቀበሌ 13 አብክመ ስፖርት ኮሚሽን ጀርባ፡፡
የአብክመ ማረ/ቤቶች ኮሚሽን