የፀፀት መልእክትን በሰውሰራሽ ክሂሎት

0
55

ቻይናውያን ወላጆች ልጆቻቸው ትዳር እንዲይዙ እና እንዲወልዱ በሰው ሰራሽ ኪሂሎት (ኤአይ) የተፈጠሩ ምስሎችን በማህበራዊ ድረ ገፆች በመልቀቅ ለማሳመን እየሞከሩ መሆኑን  ኦዲቲ ሴንትራል ድረገጽ አስነብቧል፡፡

በ2024 እ.አ.አ ስድስት ነጥብ አንድ ሚሊዬን ጋብቻዎች መፈፀማቸውን የጠቆመው የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን  ዢኒዋ ይህም ከአለፈው ዓመት 20 በመቶ ቅናሽ ያለው መሆኑን ነው ያመላከተው፡፡

ይህንኑ ተከትሎ በሀገሪቱ የሚገኙ ወላጆች እያሽቆለቆለ የመጣውን በጋብቻ የመተሳሰር እና ራስን የመተካት ልምድ መቀነስን ለመግታት መቸገራቸው ነው የተጠቆመው- በድረ ገጹ፡፡

አብዛኛው ማህብረሰብ በሚከታተለው የቻይና ዶዩን እና ዌይቦ በተሰኙ ማህበራዊ ድረ ገፆች የፀፀት ቪዲዮዎችን ወላጆች በሰውሰራሽ ክሂሎት ሲያሰራጩ መስተዋሉ ማስረጃ ሆኖ ቀርቧል፡፡

በማህበራዊ ድረ ገፆች በአዛውንቶች አምሳል የተቀረጹት በሰው ሰራሽ ክሂሎት የበለፀጉት አቀንቃኞች ወላጆቻቸው ቤተሰብ እንዲመሰርቱ በነገሯቸው ጊዜ ባለመመስረታቸው በብቸኝነት  ለመከራ መዳረጋቸውን አመላክተዋል፡፡

ለዚህም የ58 ዓመቷ ሴት ታመው በሆስፒታል ተኝተው ከጐናቸው የሚንከባከባቸው አስታማሚ ማጣታቸው በማስረጃነት ለእይታ በቅቷል፡፡

በማህበራዊ ድረ ገፆች የተለቀቁትን የፀፀት ምስሎችም ሚሊዬኖች ተጋርተዋቸዋል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የጥር 11  ቀን 2018 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here