የፍለጋዉ መጨረሻ

0
122

የህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የ47 ዓመቷ ጐልማሳ ታናሽ ወንድሟን ገድሎ የተሰወረውን ተጠርጣሪ ማንነቱን ለማወቅ እና ለማግኘት ለ27 ዓመታት ያደረገችው ክትትል በስኬት መደምደሙን ኦዲት ሴንትራል ድረ ገጽ ባለፈው ሳምንት ለንባብ አብቅቶታል፡፡

የጐልማሳዋ የ ሊሀይዩ የበቀል ታሪክ መነሻው በ1992 እ.አ.አ አባቷ ከአንድ ሰው ጋር በደሞዝ ወይም በክፍያ በተጨቃጨቁበት እለት ነበር፡፡ ጠባቸው ከሮ ስምምነት ላይ ሳይደርሱም ይቀራሉ፡፡ ክፍያ  የተነፈገው ተበዳይ ነኝ ባይ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ቂም ቋጥሮ የዘጠኝ ዓመት ታናሽ ወንድሟን ሊሁዋንፒንግ ከትምህርት ቤት ሲወጣ ጠብቆ አፍኖ ያግተዋል፡፡

የእገታ ወንጀል በታዳጊው ላይ የመፈፀሙ ሪፖርት የደረሰው የፓሊስ ኃይልም በየመንደሩ አጋቹን እና ታጋቹን ታዳጊ ለማግኘት ፍለጋውን ይያያዙታል፡፡ በሁናን ግዛት በታጋቹ መኖሪያ አካባቢ ሆኖም የሊሁዋንፒንግ  አስከሬን የተገኘው ከዓመት በኋላ ነበር፡፡ ታዳጊው በሸንኮራ አገዳ ማሳ ውስጥ በስለት ተወግቶ ተጥሎ እንደነበርም ለአባቱ ይነገረዋል፡፡

የታዳጊው ወላጅ አባት እስከ ዕለተሞቱ ድረስ ለአምስት ልጆቹ እና ለባለቤቱ ሳይነግር ማስታወሻ ፅፎ ህይወቱን ያጠፋል፡፡ በቃ እህቶቹ አንድ ቀን ወንድማቸውን ሊያገኙት እንደሚችሉም ተስፋ ይሰንቃሉ፡፡

ከእህቶቹ መካከል ሊሀይዩ በ2014 እ.አ.አ አባቷ ራሱን ሲያጠፋ ለቤተሰቦቹ የተወውን ማስታወሻ በአነበበችበት ወቅት ታናሽ ወንድሟ የደረሰበትን በሚገባ መገንዘብ ቻለች፡፡ አባቷ ለዓመታት ያደረገው ጥረት ለፍሬ አለመብቃቱን፣ አነሱን ለመጠበቅ ሲል እውነቱን መደበቁንም ተረድታ ገዳዩን ለማፈላለግ ትወስናለች፡፡

ሊሀይዩ አባቷ ስለታናሽ ወንድሟ ገዳይ ስም፣ የትውልድ ከተማ፣ ስለቁመናው ከፃፈው ማስታወሻ መረጃ አሰባስበው ገዳዩ ይገኛል ወይም ይኖራል ወደተባለበት ከተማ ታመራለች፡፡ ከዚያም ገዳዩን የሚመስል ሰው ማፈላለግ ቀጠለች፡፡ ተጠርጣሪውን እስከምታገኝ  “ስራ ፈላጊነኝ” በሚል ግንኙነት ፈጥራ ስሙን በትክክል እስከምታወቅ በመነጋገር ሦስት ዓመታትን አሳለፈች፡፡ ተጠርጣሪው ሊ ሀይዩ የታጋቹ ሟች እህት መሆኗን እንዳይጠረጥር በመጠንቀቅ ሁለት ስም እንዳለው ሲጠሩት መስማቷን ቀለል አድርጋ ትክክለኛው የቱ እንደሆነ ተጠይቀዋለች፡፡ ሁለቱም የሱ ስም መሆኑን ይነግራታል፤ ሁለት ስም ያለው አንድ ሰው፡፡

በመጨረሻም ሊ ሀይዩ ለፖሊስ አሳውቃ በሰጠቻቸው መረጃ መሠረትም ገዳዩ በ2020 እ.አ.አ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም  ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here