የ2017 የፌዴራል መንግሥት በጀት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸደቀ

0
195

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል:: ምክር ቤቱ በጉባኤውም የቀረበለትን የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን ተወያይቶ አጽድቋል:: በዚህም የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት 971 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ሆኖ ጸድቋል::

በጀቱ ምጣኔ ሀብታዊ እና ማኅበራዊ እድገትን ለማፋጠን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተመላክቷል:: የሚጸድቀውን በጀትም በሕግ እና በሥርዓት መጠቅም እንደሚገባ ተጠቁሟል:: ለዚህ ደግሞ ምክር ቤቱ የቁጥጥር እና የክትትል ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል ይጠበቅበታል ተብሏል::

ምክር ቤቱ ለ2017 በጀት ዓመት ያጸደቀው በጀት ከ2016 በጀት ዓመት በከ169 ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ አለው፤ የፌዴራል መንግሥት የ2016 በጀት ዓመት አጠቃላይ በጀት 801 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር እንደነበር ይታወሳል::

(ጌትሽ ኃይሌ)

በኲር ሐምሌ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here