የሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ ለህግ ታራሚዎች ቀለብና የምግብ ማብሰያ እንጨት፣ የደብ ልብስ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌትሮኒክስ፣ የፈርኒቸር ዕቃ እና የጽዳት እቃዎች አጠቃላይ ለመ/ቤታችን ለሥራ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ማቴሪያሎችን ለ6 ወር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 01 ሰርገኛ ጤፍ፣ ደብር ማሽላ፣ ሎት 02 ምጥን በርበሬ፣ ባቄላ ክክ ምጥን ሽሮ እና የተፈጨ ጎመን ዘር፣ ሎት 03 ፊኖ ዱቄት፣ ሎት 04 ፈሳሽ ፎር ኦል ዘይት፣ ሎት 05 የማገዶ እንጨት፣ ሎት 06 የጽህፈት መሳሪያ፣ ሎት 07 የጽዳት ዕቃ፣ ሎት 08 የደብል ልብስ፣ ሎት 09 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 10 የፈርኒቸር ዕቃ ስለዚህ ተጫራቾች ሊያሟሉት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-
የታደሰ የዘመነ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
የግብር ከፋይ መለያ ሰርፊትኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተመሰከረ /ሲፒኦ/ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ስዓት ድረስ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጅ የጨረታ ማስከበሪያ ጥሬ ገንዘብ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አይፈቀድም፡፡ ያስያዙት ሲፒኦ ከአንድ በመቶ ቢያንስ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተጫራቾች ከውድድሩ ውጭ ይሆናሉ፡፡
የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 30.00 /ሰላሳ ብር/ ደባርቅ ማረሚያ ቤት ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሒደት ቢሮ ቁጥር 03 መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች በሚቀርቡት መወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ሥርዝ ድልዝ ካለው ፓራፍ መደረግ አለበት፡፡ ጨረታው 23/03/2017 ዓ.ም እስከ 7/04/2017 ዓ.ም ከደባርቅ ማረ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን በ 16ኛው ቀን 3፡00 ይታሸጋል፡፡ ጨረታው በቀን 08/04/2017 ዓ.ም በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የካላንደር በዓል ቢሆን በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው ተጫራቾች ማንኛውንም መረጃ ፎቶ ኮፒ አባሪ በማድረግ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ጨረታው የሚለየው በሎት ዋጋ ይሆናል ተጫራቹም ሁሉንም ዕቃዎች መሙላት አለበት፡፡
አሸናፊው ተጫራች እቃውን የሚያስረክበው ሰ/ጎ/ዞን/ ማረ/ቤቶች መምሪያ ድረስ ይሆናል፡፡
ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሃያ አምስት በመቶ ማስያዝ የሚችሉ፡፡
ሎት O5፣ 06 እና 09 ላይ የተዘረዘሩት ዕቃዎች የግዥ መጠን ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መጥተው ውል መውሰድ የሚችሉ፡፡
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መ/ቤቱ የሚገዛውን ዕቃ ሃያ በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በሥልክ ቁጥር 058 117 04 19 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰሜን ጎንደር ዞን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ