ድርሰት ከድርሰትነት ባለፈ ለችግሮች መውጫ መንገድን ጠቋሚ ሊሆኑ ይገባል

0
205

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋዜጠኛው አባትሁን ዘገየ “ስደተኛው ብዕር” የተሰኘ የልቦለድ መጽሐፍን በማስመረቅ ለንባብ አብቅቷል::

በመጽሐፉ ምረቃ ወቅት የተገኙት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተለያዩ የስራ ባልደረቦች መጽሐፉ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሐብታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ትኩረት ሰጥቶ የዳሰሰ መሆኑን አንስተዋል:: ደራሲው ለስነ ጽሑፍ ካለው እምቅ አቅም እና ዝንባሌ አኳያ እስካሁን መዘግየቱን ጠቁመው፣ በቀጣይ በርካታ ሥራዎችን እንደሚጠብቁ ጠይቀዋል::

የመጽሐፉ ደራሲ ጋዜጠኛ አባትሁን ዘገየ ድርሰቶቹ ደራሲዉ አሁን የኖረባቸውን፣ እየኖረባቸው ያሉትን እና የወደፊቱን የሚያስታውሱ እና የሚያስመለክቱ ይዘቶች እንደተካተቱበት ገልጿል::

“አሁን ያለንበት ዘመን በበርካታ ምስቅልቅሎች ይገለጻል” ያለው ደራሲ እና ጋዜጠኛ አባትሁን ዘገየ፣ በመጽሐፉ ውስጥ የተካተቱ ጭብጦች ቢተገበሩ ኢትዮጵያን አሁን ከገባችበት ቀውስ ለማውጣት ትልቅ አቅም እንደመሆኑ እምነታቸው መሆኑን ገልጸዋል::

ድርሰቶቹ ከድርሰትነት ባለፈ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሐብታዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በጥልቀት የቃኙ መሆኑንም ተመላክቷል:: ሀገር ሰላሟ ተጠብቆ በሕዝቧ ከከፍታ ማማ ላይ የምትወጣው ከቤተሰብ ጀምሮ ያሉብንን ችግሮች በስክነት እና በመደማመጥ የመፍታት ልምድ ሲዳብር እንደሆነ ደራሲዉ አመላክቷል:: ስደተኛው ብዕር እንደ ሀገር ያሉ ልዩነቶችን ለመፍታት ትምህርት የሚሰጥ እንደሆነም ጠቁሟል::

 (ስማቸው አጥናፍ)

በኲር ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ዕትም

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here