የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዳባት ወረዳ አሰተዳደር ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በካፒታል በጀት የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ በዳባት ከተማ በቀበሌ 04 በሚገኘዉ ቦታ ላይ በሙሉ ዋጋ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ እና 2018 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያደሱ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ የሆኑ፡፡
- በዘርፉ ፈቃድ ያላቸው ደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፡፡
- ጨረታው ሲሞላ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ በመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-6 የተጠቀሱትን እና ሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ዋና እና ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ድጋፊ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ ብር አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዛ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና መስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን ዋና እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ አጠቃሎ በማሸግ ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ድጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 ጋዜጣዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በተከታታይ 15 ቀናት የካቲት 02/2018 እስከ የካቲት 16/2018 ዓ/ም ድረስ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/አስ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 በቀን የካቲት 17/2018 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ብሔራዊ በዓል እና ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ይከፈታል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የቴክኒካል እና ፋይናሽያል በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ሊገዙ ሲመጡ ፈቃዳቸዉን ሰነድ ለሚሸጠዉ ረ/ገንዘብ ያዥ እያሳዩ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻ ለረ/ገንዘብ ያዥ መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዳ/ወ/ግ/ፋ/ን/እስ/ ድጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 113 02 05 ወይም 058 113 04 10 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዳባት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

