ገዳዮቹ መጫዎቻዎች

0
57

የጃፓን ባለስልጣናት በሀገሪቱ የሚገኙ ከ16 ሺህ የሚበልጡ መጫዎቻ ሽጉጦች ጥይት ጐርሰው ጉዳት ማድረስ እንደሚችሉ ተረጋግጦ፤ ማንኛውም በእጁ የሚገኝ ዜጋ በአስቸኳይ ለፖሊስ ማስረከብ እንደሚኖርበት ማሳሰቢያ መሰጠቱን ኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ  አስነብቧል፡፡

የጃፓን ብሔራዊ የፓሊስ ተቋም እንደገለፀው የመጫዎቻ ሽጉጦቹ ከእስያ ሀገራት ተመርተው ወደ ጃፓን የገቡ ናቸው። አቅማቸውን  ፈትሾም ትክክለኛውን የሽጉጥ ጥይት ጐርሰው ጉዳት ማድረስ እንደሚችሉ አረጋግጧል፡፡ ለኢላማ ልምምድ ወይም ውድድር የሚውሉት እና በሽልማት የሚበረከቱት ሽጉጦቹ በስሪታቸው በ(ሪቮልቨር) የጥይት ካዝና  ትክክለኛውን ጥይት ጐርሰው ጉዳት ማድረስ ይችላሉ።

 

የመጫዎቻ ሽጉጦቹ አሻንጉሊትን “አርቲፊሻል” ትክክለኛ ጥይት መሳይ ተተኳሽን  ጐርሰው ዒላማ ለመምታት የተመረቱ ቢሆኑም በፓሊስ ምርመራ የጥይት መውጊያውም ሆነ ጥይት መያዣ ከፍተቶቹ እውነተኛውን ጥይት ጐርሰው ጉዳት ማድረስ ይችላሉ፡፡

በፖሊስ ምርመራ መሰረት ከውጪ ተሰርተው ወደ  ጃፓን ከጉቡት መካከል 16ቱ መጫዎቻ ሽጉጦች  ገዳይ ጥይትን መተኮስ ይችላሉ።

መጫዎቻ መሰሉን ገዳይነቱ የተረጋገጠውን “አርቲፊሻል” ሽጉጥ ይዞ መገኘት በጃፓን የሰይፍ እና ገዳይ ጦር መሣሪያ ቁጥጥር ህግን የሚጥስ መሆኑም ነው የተብራራው፡፡

ፖሊስ ባደረገው የማጣራት ስራ ካለፈው 2024 ታህሳስ ወር ወዲህ  በመጫዎቻ ሽጉጥ መልክ በውጪ ሀገር የተመረቱ “ሽጉጦች” ባስመጪ ኩባንያው መሰረት በ31 ግዛቶች ለ78 የሀገር ውስጥ አከፋፋዮች ተሰራጭቷል፡፡

 

(ታምራት ሲሳይ)

በኲር የሐምሌ 28  ቀን 2017 ዓ.ም ዕትም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here