በሰሜን ጎጃም ዞን የይልማና ዴንሳ ወረዳ ገንዘብ ኢ/ትብ/ጽ/ቤት ለይ/ዴ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ ሎት 1 የኤሌክትሮኒከስ፣ ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ ጨረታ፣ ሎት 2 የይ/ዴ/ወ/መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት የመንገድ ሥራ የማሽን ኪራይ ማለትም ከአዴት መንደረ-እየሱስ ቀበሌ መንገድ ለማሰራት የማሽን ኪራይ፣ ሎት 3 የይ/ዴ/ወ/ግብርና ጽ/ቤት የኮንች ቀበሌ የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ እና ሎት 4 የውሃ ግንባታ እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት፣ መንገድ ማሰራት እና ግንባታ ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ተጫራች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የቲን ተመዝጋቢ መሆናቸዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በዘርፉ አግባብ ያለዉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የኤሌክትሮኒከስ እና የውሃ ግንባታ እቃ ግዥው ከብር 200‚000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታዉ መሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ተጨማሪ ማስረጃ ቢያስፈልጋቸዉ የይ/ዴ/ወ/ገ/ኢ/ትብ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም በስልክ ቁጥር 058 338 02 98 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሂሳብ የኤሌክትሮኒከስ ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ሲሆን ፣ የመንገድ ሥራው የማሽን ኪራዩ ብር 85,000 (ሰማንያ አምስት ሽህ ብር) ብቻ፣ የውሀ ግንባታ እቃ ብር 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) ብቻ እና የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታው ብር 50,000 (አምሳ ሽህ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከዋና ገንዘብ ያዥ አስይዘዉ ለግዥ ኦፊሰሮች ማስመዝገብ ይኖርባቸዋል ወይም በባንክ የተረጋገጠ (ሲፒኦ) ከሆነ ከፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ማሸግ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ካለ ከአሸናፊዉ ዋጋ ጋር ተደምሮ ሲያዝ የተሸነፈዉ ተጫራች የሚያስይዘዉ ገንዘብ ይመለስላቸዋል፡፡
- ጨረታዉ የሚከፈትበት ዕለት በበዓል ቀናት ከሆነ ወደ ቀጣዩ የሥራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
- የኤሌክትሮኒከስ እና የውሃ ግንባታ እቃ ጨረታ ሰነዱን ከታህሳስ 27/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 11/2018 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት እና የመንገድ ሥራ የማሽን ኪራይ እና የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታው ጨረታ ሰነዱን ከታህሳስ 27/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 17/2018 ለ21 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የተሞላበትን ፎርም ቲን፣ የንግድ ፈቃድዎንና ሌሎች ያልተጠቀሱ ማስረጃዎችን በታሸገ ፖስታ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የኤሌክትሮኒከስ እና የውሀ ግንባታ እቃ ጨረታዉ የሚዘጋበት ጥር 12/2018 ዓ.ም በ3፡30 ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተዉ ጥር 12/ 2018 ዓ.ም በ4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ፍላጎት ያላቸዉ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እና የመንገድ ሥራው የማሽን ኪራይ እና የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ /ጨረታዉ የሚዘጋበት ጥር 18/2018 ዓ.ም በ3፡30 ሲሆን ጨረታዉ የሚከፈተዉ ጥር 18/2018 ዓ.ም በ4፡00 ቢሮ ቁጥር 3 ፍላጎት ያላቸው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በጨረታዉ መክፈቻ ዕለት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታዉን ለመክፈት የሚገድበዉ ነገር የለም፡፡
- አሸናፊ አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ 10 በመቶ የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አሸገዉ ከሚያስገቡት ሰነድ እና ፖስታ ላይ አድራሻና የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ጨረታዉን የምናወዳድረዉ በሎት (በጠቅላላ) ዋጋ ነዉ፡፡
- ግዥ ፈጻሚ አካል ያሸነፈውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ እንዳስፈላጊነቱ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- የሚሞላው ዋጋ ማንኛውንም ታክስ ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ጨረታዉ ለ40 ቀናት ጸንቶ ይቆያል፡፡
- የኤሌክትሮኒከስ እና የውሃ ግንባታ እቃ ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት እያንዳንዱ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ ነዉ፡፡
- የመንገድ ሥራው የማሽን ኪራይ እና የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከል ግንባታ ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ብር 400 (አራት መቶ ብር) ብቻ ነዉ፡፡
- የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከል በግባታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች /ተጫራቾች/ ደረጃ 6 እና በላይ መሆን አለባቸው፡፡
የይልማና ዴንሳ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

