ግልጽ የሊዝ  ጨረታ ማስታወቂያ

0
84

በደቡብ ጎንደር ዞን በታች ጋይንት ወረዳ በአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2017 በጀት አመት በከተማው ውስጥ የሚገኙትን የመኖሪያና የድርጅት ቦታዎች በአዋጅ ቁጥር 721/2004 በደንብ ቁጥር 103/04 አንቀጽ 13/2 በመመሪያ ቁጥር 1/2005 አንቀጽ 17 በሚያዘው መሰረት አጫርቶ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ አርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ በብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ የማይመለስ ገዝታችሁ መጫረት የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ፖስታው ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 25/09/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በ10ኛው ቀን 06/10/2017 ዓ.ም እስከ 11፡30 ድረስ ታስገቡና  በዚሁ ቀን በ11፡30 ላይ ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት በ11ኛው ቀን 09/10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ላይ አርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ4፡00 ይከፈታል፤ ተጫራቾች  ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም  ባይገኙም ፖስታው ይከፈታል፡፡ ተቋሙ ጨረታውን ካልተስማማበት በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳስባለን፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 268 02 05 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአርብ ገበያ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here