የሰሜን ወሎ ዞን የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ ጽ/ቤት የሊዝ ቦታ ጨረታ ኮሜቴ የከተማ ቦታን በሊዝ ሰለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ቁጥር ከሀ እሰከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ከሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ ማወቅ እና የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል በመሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ተ.ቁ | የጨረታዉ አይነት | የጨረታዉ ዙር | የቦታዉ መገኛና ቀበሌ | የቦታዉ ስፋት | የቦታዉ አገልግሎት | ለቦታዉ የተሰጠዉ የጨረታ ኮድ ቁጥር |
1 | መደበኛ | 3ኛ ዙር | 02 ቀበሌ አህመድ ስሪንቃ ቤት ጀርባ | 150.75 | ለተለያዩ የኢንቨስትመንት አገ/ቶች
|
01 |
2 | መደበኛ
|
›› | 02 ቀበሌ ሀቫና ፊት ለፊት | 147 ካ.ሜ | ለተለያዩ የኢንቨስትመንት አገ/ቶች
|
02 |
3 | ›› | ›› | 02 ቀበሌ ቡና ባንክ ጀርባ | 172.02 ካ.ሜ | ለተለያዩ የኢንቨስትመንት አገ/ቶች | 03 |
4 | ›› | ›› | 02 ቀበሌ ገበያዉ ዳር የዱሮዉ ፖሊስ ጣቢያ የነበረዉ | 570 ካ.ሜ | ለተለያዩ የኢንቨስትመንት አገ/ቶች | 04 |
5 | ›› | ›› | 01 ቀበሌ ከቴሌዉ አካባቢ | 534.6 ካ.ሜ | ለተለያዩ የኢንቨስትመንት አገ/ቶች | 05 |
6 | ›› | ›› | 03 ቀበሌ ሀብሩ ወረዳ ጽ/ቤት ፊት ለፊት | 1727 ካ.ሜ | ለተለያዩ የኢንቨስትመንት አገ/ቶች | 06 |
- የጨረታው ዙር፡- የ2017 ዓ.ም፣
- የጨረታው ዓይነት፡- መደበኛ፣
- ቦታው ከማንኛውም ክርክር ነፃ ነው፣
- የቦታው ደረጃ 1ኛ፣
- በቦታው የሚፈቀደው አገልግሎት አይነት የህንፃው ከፍተኛ የግንባታ ወለል ግቢ ስፋት ንጽጽር በፕርስንት ሆኖ ቦታው ለተለያዩ ኢንቨስትመንት (ለሆቴል ፣ለምግብ አዳራሽ ለምኝታ አገልግሎት) የሚውል ሲሆን ከፍታውም G+4 ፎቅና ከዚያ በላይ ሆኖ 70 በመቶ የቦታው ስፋት በግንባታ ይሸፈናል፡፡
- የጨረታው መነሻ የሊዝ ዋጋ ለ1 ካሬ 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ ነው፡፡
- የሚፈለገው አነስተኛ የቅድሚያ ክፍያ መጠን አጠቃላይ የቦታውን ዋጋ 20 በመቶ ይሆናል፡፡
- የቀሪ ክፍያ ማጠናቀቂያ መጀመሪያ ክፍያ ከተከፈለበት ከ2 ዓመት የእፎይታ ጊዜ በኋላ ጀምሮ እሰከ ሊዝ ዘመኑ 40 አመት (አርባ) ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፍ እንደተገለፀለት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ዋጋ ከ20 በመቶ ያላነሰ ቅድሚያ ክፍያ ወይም በቴክኒካል ፕሮፖዛሉ ላይ የገለፀውን ቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም ውል ይፈፀማል፡፡ በተጠቀሰው ቀን በሚሰጠው ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ 2ተኛ የወጣው አንደኛ የወጣውን ዋጋ በመስጠት መውሰድ ከፈለገ ይሰጠዋል፡፡
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ የተጫረተበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማብዛት የሚገኘውን ውጤት 5 በመቶ ያላነሰ በኦርጅናል ፖስታ ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቹ የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በማድረግ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ታሽጎ በጽሁፍ ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የቦታ ዋጋ በፊደልና በአሀዝ መሙላት ይኖርበታል፡፡ በፊደልና በአሀዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፌደል የተፃፈው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይቻልም ገዝቶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄድበት ጊዜ ከ23/10/2017 ዓ.ም እስከ 02/11/2017 ዓ.ም በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
- በሰነድ ማሳሰቢያው ሀሳብ ላይ በፊደልና በአሀዝ የተፃፈው ሥርዝ ድልዝና የሚያምታታ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- የጨረታው የሰነድ ሽያጭ የሚያልቅበት 02/11/2017 ዓ.ም ክቀኑ 9፡00 ላይ ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ እና የጨረታ ሀሳብ ማቅረቢያ ቅፅ እንድሁም የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ እና ሌሎች ሰነዶችን በማሸግ አስከ 11፡00 ወደ ጨረታ ሳጥን ገቢ ያደርጉና ሳጥኑ የሚታሸግ ይሆናል፡፡
- ሰነዱን በመሬት ልማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት) በመምጣት በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
- ቦታውን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በማንኛውም የሥራ ስዓት በአካል በመቅረብ የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው 03/11/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 በመርሳ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥራችን 033 333 00 68 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ በጨረታው ካልተስማመ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመርሳ ከተማከ/መ/ል/ጽ/ቤት