በሰሜን ወሎ ዞን የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ ጽ/ቤት የሊዝ ቦታ ጨረታ ኮሚቴ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ቁጥር ከ ሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሰረት ለኢንቨስትመንት አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ከመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ ማወቅ እና የጨረታ እና የጨረታ ሰነድ ለመግዛት የማይመለስ ብር 600 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል በመሬት ልማትና አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
ተ.ቁ | የጨረታው ዙር | የቦታው መገኛና እና ቀበሌ | የቦታው ስፋት | የቦታው አገልግሎት | የጨረታ ኮድ ቁትር |
1 | 1ኛ ዙር | መርሳ 01 ቀበሌ ከቴሌው በስከ ደቡብ አቅጣጫ | 472 ካ.ሜ | ለኢንቨስትመንት አገ/ቶች/ ሆቴል | 01 |
2 | 1ኛ ዙር | መርሳ 01 ቀበሌ ከቴሌው በስከ ሰሜን አቅጣጫ | 444.4 ካ.ሜ | ለኢንቨስትመንት አገ/ቶች/ ሆቴል | 02 |
3 | 1ኛ ዙር | መርሳ 03 ቀበሌ ህብሩ ወረዳ ጽ/ቤት ፊት ለፊት | 1727 ካ.ሜ | ለኢንቨስትመንት አገ/ቶች/ ሆቴል | 03 |
4 | 1ኛ ዙር | 03 ቀበሌ አቧራ ቡሆሮ መገንጠያ ገባ ብሎ | 2626 ካ.ሜ | ለጤና ተቋም አገልግሎት | 04 |
- የጨረታው ዙር፡- የ2018 ዓ.ም 1ኛ ዙር
- የጨረታው ዓይነት፡- መደበኛ
- ቦታው ከማንኛውም ክርክር ነፃ የሆነ
- የቦታው ደረጃ 1ኛ
- በቦታው የሚፈቀደው አገልግሎት አይነት የህንፃው ከፍተኛ የግንባታ ወለል ግቢ ስፋት ንጽጽር በፕርስንት ሆኖ ቦታው ለተለያዩ ኢንቨስትመንት ለሆቴል ፤ለምግብ አዳራሽ ለመኝታ አገልግሎት የሚውል ሲሆን ከፍታውም G+4 ፎቅና ከዚያ በላይ ሆኖ 70 በመቶ የቦታው ስፋት በግንባታ ይሸፈናል፡፡
- የጨረታው መነሻ የሊዝ ዋጋ ለ1 ካሬ 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ፡፡
- የሚፈለገው አነስተኛ የቅድሚያ ክፍያ መጠን አጠቃላይ የቦታውን ዋጋ 20 በመቶ ይሆናል፡፡
- የቀሪ ክፍያ ማጠናቀቂያ የመጀመሪያ ክፍያ ከተከፈለበት 2 ዓመት የእፎይታ ጊዜ በኋላ ጀምሮ እሰከ ሊዝ ዘመኑ 40 አመት ይሆናል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ እንደተገለፀለት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ የጨረታውን ዋጋ ከ20 በመቶ ያላነሰ ቅድሚያ ክፍያ ወይም በቴክኒካል ፕሮፖዛሉ ላይ የገለፀውን ቅድሚያ ክፍያ በመፈፀም ውል ይፈፀማል፤ በተጠቀሰው ቀን በሚሰጠው ጊዜ ያልቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል፤ 2ተኛ የወጣው አንደኛ የወጣውን ዋጋ በመስጠት መውሰድ ከፈለገ ይሰጠዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) የተጫረተበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማብዛት የሚገኘውን ውጤት 5 በመቶ ያላነሰ ፖስታ ውስጥ ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቹ የሚያቀርበው የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ በማድረግ በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ታሽጎ በጽሁፍ ለይቶ ማቅረብ አለበት፡፡
- በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የቦታ ዋጋ በፊደልና በአሀዝ መሙላት ይኖርባቸዋል፤ በፊደልና በአሀዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፌደል የተፃፈው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
- አንድ ተጫራች ለአንድ ቦታ ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይቻልም፤ ገዝቶ ከተገኘ ክጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚካሄድበት ጊዜ ከመስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
- በሰነድ ማሳሰቢያው ሀሳብ ላይ በፈደልና በአሀዝ የተፃፈው ሥርዝ ድልዝና የሚያምታታ ከሆነ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- የጨረታው ሰነድ ሽያጭ የሚያልቅበት መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ክቀኑ 9፡00 ላይ ሲሆን ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ እና የጨረታ ሀሳብ ማቅረቢያ ቅፅ እንድሁም የጨረታ ማስክበሪያ (ሲፒኦ) እና ሌሎች ሰነዶችን በማሸግ አስከ 11፡00 ወደ ጨረታ ሳጥን ገቢ ያደርጉና ሳጥኑ የሚታሸግ ይሆናል፡፡
- ሰነዱን በመሬት ልማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ቦታውን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በማንኛውም የሥራ ስዓት በአካል በመቅረብ የምናስጎበኝ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው መስከረም 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 በመርሳ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፡፡
- መስሪያ ቤቱ በጨረታው ካልተስማሙ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ወይም ማብራሪያ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 033 333 00 65 በመደወል መረጃ መጠየት ይችላሉ፡፡
የመርሳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት