በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ለብዙ ጊዜያት የቆዩ በውስጡ ያሉትን የተለያዩ አገልግለው የተመለሱ የተቆራረጡ ብረታ ብረት፣ አልጋ እና ኮንቲነር በሐራጅ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ተወዳዳሪ እንዲወዳደር ይጋብዛል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዚጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚሸጡ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት መተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥና ፋይናንስ ቢሮ መግዛት ወይም መግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ ባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ወይም በጥሬው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ከ13/12/2016 ጀምሮ እስከ 27/12/2016 ዓ.ም ድረስ መውሰድ እና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም በ 28/12/2016 ጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል ግዥና ፋይናንስ ቢሮ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዋጋ ሲሆን መሥሪያ ቤቱ የተሸላ አማራጭ ካገኘ በሎት አሸናፊ የመለየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ድርጅቱ በምዕራብ ጎንዳር ዞን ፍትህ መምርያ ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና እቃዎችን በራሱ ወጭ ከመተማ ሆስፒታል የንብረት መጋዘን በዝርዝር መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዘር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 331 03 38/058 331 01 75 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው እቃውን ከገዛበት ወይም እቃው ከተሸጠበት ከ5 ቀን በኋላ ካላነሳ የመጋዝን ኪራይ ይከፍላል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ ከተጠየቀው ጠቅላላ እቃ አቅረቦት ሃያ በመቶ ከፍ ወይም ዝቅ ማለት ይችላል፡፡
- ተጫራቾች እቃዎችን በሚገኙበት ቦታ ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በትክክል ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት መሙላትና በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ የተወዳዳሪ ስም፣ አድራሻ፣ ፊርማ እና ስልክ ቁጥር በማስቀመጥ የፖስታውን ኦርጅናል እና ኮፒ በመለያት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል