በአፈ/ከሳሽ አጋሉ ወንድም እና በአፈ/ተከሳሽ ዘለቀ አምናየ መካከል ስላለዉ የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ በእጅባራ ከተማ 05 ቀበሌ አዋሳኙም በምሥራቅ ክፍት ቦታና ፀጋየ ታየ ፣በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን መንገድ ፣በደቡብ መንገድ ተዋስኖ የሚገኝ ንብረትነቱ አፈ/ተከሳሽ ዘለቀ አምናየ ንብረት የሆነ ቤት በመሻ ዋጋ 2,340,847 /ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ አርባ ሺህ ስምት መቶ አርባ ሰባት ብር/ በማድረግ የጨረታዉ ማስታወቂያዉን 30 ቀን በተከታታይ በአየር ላይ እንዲቆይ በማድረግ የካቲት 07 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ ከ3፡00 እስከ 5፡00 ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልሁ ሁሉ የግምቱን 1/4ኛዉን በማስያዝ እና በቦታው በመገኘት መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡
የአዊ ብሔ/አስ/ከፍ/ፍ/ቤት