ግልጽ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

0
112

በአፈ/ከሳሽ ዘንገና እቁብ ማህበር አፈ/ተከሳሽ ተገኘ ጫኔ መካከል ባለው የገንዘብ ክርክር ጉዳይ በእንጅባራ 01 ቀበሌ በአዋሳኝ በምሥራቅ 022 ፣በምዕራብ መንገድ ፣በሰሜን 014፣ በደቡብ 012 መካከል የሚገኘውን በአቶ ተገኘ ጫኔ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መኖሪያ ቤት /የድርጅት/ ቤት በመነሻ ዋጋ 2,360100 /ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ስልሳ ሺህ አንድ መቶ ብር/ ስለሚሸጥ መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራች ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከ7፡00 እስከ 10፡00 ንብረቱ ባለበት እንጅባራ ከተማ 01 ቀበሌ ቦታው ድረስ በመቅረብ መጫረት የምትችሉ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች ወደ ጨረታው ሲመጡ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 /በሲፒኦ/ የተረጋገጠ ሰነድ ይዘው በመምጣት እንድትጫረቱ ሲል ፍ/ቤቱ አዝዟል፡፡

የባንጃ ወረዳ ፍርድ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here