በአፈ/ከሣሽ 1ኛ በእውቀት በላይ 2ኛ. እናት ፈንታ አላምነህ እና በአፈ ተከሣሽ አለምነህ ይስማው መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በአገው ግምጃ ቤት ከተማ 01 ቀበሌ አዋሣኝ በምሥራቅ ወ/ሮ ቢተውሽ ሽሻው ፣በምዕራብ አየነው ካሳሁን ፣በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ክፍት ቦታ መካከል የሚገኘው በ500 ካሬ ሜትር ላይ የተሰራ የተከሣሽ ቤት አሁን ካለው የከተማ ማስተር ፕላን ጋር የማይጣጣም ነው በሚል የፕላን ማስተካከያ ተጠይቆበት የአለ እና ማስተካከያው ተግባራዊ እስከሚሆን ስመ-ንብረቱ ወደ ገዥው ሳይዞር እንደሚቆይ ታውቆ በመነሻ ዋጋ 581,698.80 /አምስት መቶ ሰማኒያ አንድ ሽህ ስድስት መቶ ዘጠና ስምንት ብር ከሰማኒያ ሣንቲም በማድረግ ጨረታውን ከታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ የካቲት 07 ቀን 2017 ዓ.ም በአየር ላይ በማዋል ጨረታው የካቲት 08 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልጉ ሁሉ በቦታው ተገኝቶ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል፡፡
የአዊ /ብሔ/ዞን/ከፍ/ቤት