በፍ/ባለመብት ሕብረት ባንክ እና በፍ/ባለ ዕዳ አቶ ማማሩ ምስለኔው መካከል ስለአለው የአፈፃፀም ክስ ክርክር ጉዳይ የባለዕዳው ንብረት የሆነውን በፍ/ሰላም ከተማ ቀበሌ 02 ክልል ውስጥ የሚገኘውን የፍርድ ባለዕዳውን ንብረት የሆነውን በአዋሳኘ በምሥራቅ አብርሃም ፣በምዕራብ መኮነን በቀለ ፣በሰሜን ባይህ ፀሐይ እና በደቡብ መንገድ የሆነው በካርታ ቁጥር 5666/2008 የተመዘገበ በግምቱ መነሻ ዋጋ ብር 1,850,000 /አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሀምሳ ሺህ ብር/ ሆኖ ሃምሌ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡30 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በግልጽ ጨረታ ይሸጣል፡፡ ስለዚህ የባለዕዳውን ንብረት በጨረታ መግዛት ለምትፈልጉ ሁሉ ከላይ በተጠቀሰው ቦታና ሰዓት በመገኘት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አሸናፊው እንደታወቀ የሽያጭ ገንዘብ ውስጥ ቢቻል ሙሉውን ካልተቻለ ¼ ኛውን በምዕ/ጎጃም ዞን ከ/ፍ/ቤት አካ/ቁጥር በሞዴል 85 የሚያስይዝ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የምዕ/ጎጃም ዞን ከ/ፍ/ቤት