ግልጽ የጨረታ ማሰታወቂያ ቁጥር 01

0
95

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው  ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች ከተመደበላቸው የሥራ ማስኪያጃ በጀት ውስጥ የተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የመንገድ ጥገና የማሽን ኪራይ፣ ሎት 2. የተለያዩ የመኪና እቃዎች፣ ሎት 3 የመኪና ጎማና ካላማዳሪ ሎት 4. የተለያዩ የስፖርት ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዛውን እቃ ዝርዝርና የመንገድ ጥገና የማሽን ኪራይ አይነቶችን መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን ሳምፕል ናሙና የሚጠይቁትን እቃዎች ናሙና ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ማየት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት00 /ሃምሳ ብር/ በኢትዩጵያ ንግድ ባንክ በአነደድ ወረዳ የወረዳ በጀት ማስፈጸሚያ አካውንት ቁጥር 1000091375048 በማስገባት ደረሰኙን በማቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማሰከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጥቅል ዋጋ ለሎት ብር 10000.00 /አስር ሽህ ብር/ ለሎት 2. ብር 4500.00 /አራት ሽህ አምስት መቶ ብር/ ለሎት 3. ብር 4000.00 /አራት ሽህ ብር/ ለሎት ብር 4. ብር 3000.00 /ሶስት ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አለዚያም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አነደድ ወረዳ የወረዳ በጀት ማስፈጸሚያ አካውንት ቁጥር 1000091375048 ላይ ገቢ አድርጎ ሰነዱን አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም በሁለት ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስሙን ፤ፊርማውንና ማህተሙን በማሳረፍ አነደድ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ግቢ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘውትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀንና እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የሥራ ቀን ካልሆነም በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ወቅት  በሰዓቱ ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት  አለው፡፡ በጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት ያልተገኙ ተወዳዳሪዎች በተላላፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  8. አሸናፊው አካል ያሸነፈባቸውን እቃዎች ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን መ/ቤቱ ከሚፈልግበት ቦታ አነደድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ድረስ የማቅርብ ግዴታ ያለበት ሲሆን በሎት 1 አሸናፊ የሆነው አካል ደግሞ የጥገና ሥራው ከሚከናወንበት ቦታ ድረስ ሙሉ ወጭውን ችሎ ማቅረብ አለበት፡፡ እንዲሁም ለውል መያዣ የሚፈለጉ ወጭዎችን አሸናፊው አካል የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  9. ግዥ ፈጻሚው አካል ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን በጨረታው መሰረዝ ምክንያት ለወጣው ወጭ መ/ቤታችን ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  10. ውድደሩ በሎት ስለሚታይ ተጫራቾች በአንድ ሎት ያሉትን ዝርዝር እቃዎች ሁሉንም ዋጋ መሙላት ያለባቸው ሲሆን ግዥ ፈጻሚው አካል ካወጣው ስፔስፊኬሽን ውጭ በራሱ ስፔስፊኬሽን የሞላ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
  11. በውድድሩ አሸናፊ የሆኑ ተወዳደሪዎች ያሸነፉበትን እቃ ወይም የመንገድ ጥገና ሥራ በሚመለከተው ባለሙያ የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
  12. የሎት 01 አሸናፊ የሆነው ድርጅት ለማሽን የሚያስፈልገውን ናፍጣ ራሱ አሸናፊው የሚችል ይሆናል፡፡
  13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለገ አነ/ወ/ሲ/ሰ/ጽ/ቤት ውስጥ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በአካል ማግኘት ቁጥር ወይም በስልክ ቁጥራችን 09 13 27 18 23 /09 46 08 84 03 በመደወል ይችላሉ፡፡

የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here