በደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2018 በጀት አመት ሎት 1 የሆስፒታሉ ህንፃዎች እድሳት (ጥገና) አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም ድርጅት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለበት፡፡
- የመታደሻ ወቅቱ ያላለፈበት ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ አምሰት መቶ ሽህ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የሚስራው ሰራ (የጥገናው) ዝርዝር በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፍል ቢሮ ቁጥር 25 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸዉ የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደተጫራቹ ምርጫ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት/ በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 የሚያዝ ሆኖ የጠቅላላ ግዥዉን ፕርስንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሽናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ዋጋ 25 በመቶ በመክፈል ውል መያዝ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በታሸገ ፖስታ በአ/የመ/ደ/ሆ/በግ/ፋ/ንአስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 25 ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ ካሸናፊ ድረጅት ያሸነፋቸውን እቃዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመር የመቀነሰ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ በግ/ፋ/ን አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 25 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ነው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ጨረታውን የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን ይከፈታል፡፡
- ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ ዋጋው ነው፡፡
የአንዳቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

