የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የስራና ክህሎት ቢሮ የምሥራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ የአማኑኤል ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያን፣ ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን፣ ሎት 3. የጽዳት እቃዎችን ሎት 4. የግብርና እቃዎችን፣ ሎት 5. የእንስሳት መዳኒት /የህክምና እቃዎችን፣ ሎት 6. የኮንስትራክሽን (ህንፃ መሳሪያዎችን) ደንጋይ፣ አሽዋ እና ጠጠርን ይጨምራል፣ ሎት 7. የልብስ ስፌት እቃዎችን፣ ሎት 8. የኤሌክትሪክ እቃዎችን፣ ሎት 9. የዶሮ መኖዎችን እና ሎት 10. ህትመቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማራ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሠነዱ ማግኙት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲሆን በ16ኛው ቀን እስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በዓል ቢሆን በቀጣይ የሥራ ቀን እና ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አማኑኤል ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ ግዥና ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በየሎቱ ጠቅላላ ድምር ይሆናል፡፡
- የጨረታ አሸናፊው ያሸነፈባቸውን እቃዎች አማኑኤል ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ ማድረስ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በአካል በመገኙት ወይም በስልክ ቁጥር 058 777 03 71 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የግዥ አፈፃፅም መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
አማኑኤል ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ

